1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካ የምትከተለው የአፍሪቃ ፖሊሲ

ሰኞ፣ ሰኔ 17 2005

ባራክ ኦባማ እስካሁን ለአፍሪቃ ምን አስተዋፅዎ አድርገዋል? በቀራቸው የስልጣን ዘመንስ በአፍሪቃ የሚታወሱበት ምን ትተው ማለፍ ይችሉ ይሆን?በዚህ ውይይት ላይ የተነሱ ሀሳቦች ናቸው።

https://p.dw.com/p/18ujR
US President Barack Obama (R) smiles as he walks with First Lady Michelle Obama (2nd L) through a line of dancers during a departure ceremony in Accra, Ghana, July 11, 2009. AFP PHOTO/Jim WATSON (Photo credit should read JIM WATSON/AFP/Getty Images)
ምስል AFP/Getty Images

የዮናይትድ እስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጀርመንን ብቻ ጎብኝተው ማብቃት የፈለጉ አይመስልም። በሚመጣው ሳምንት ወደ አፍሪቃ ይጓዛሉ። እዛም ሶስት ሀገራትን፤ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪቃ እና ታንዛንያን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በባራክ ኦባማ በፕሬዚዳንትነት መመረጥ በርካታ አፍሪቃውያን መደሰት ብቻ ሳይሆን ትንሽም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ ለጥቁሮች አህጉር አፍሪቃም ይተርፋሉ ብለው ተስፋ ጥለውባቸው ነበር። ባራክ ኦባማ ስልጣን ከያዙ ካለፉት 5 ዓመታት ወዲህ ለመሆኑ ዮኤስ አሜሪካ የምትከተለው የአፍሪቃ ፖሊሲ ምን ይመስላል? የዛሬው የእንወያይ ዝግጅት ርዕስ ነው። የዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ውይይቱን መርቷል።

አበበ ፈለቀ

ልደት አበበ