1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሜሪካ የመሪነት ሚናዉን ዉሰጂ!

ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 2002

በኢትዮጵያ የአየር ጠባይ ለዉጥ ለሚያስከትለዉ ችግር መፍትሄ ይመጣ ዘንድ በዚንዱስትሪ የበለፀጉ አገራት ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ እየተጠየቀ ነዉ። ሰሞኑን የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ የጀመረዉ አሜሪካ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ አገሪቱ በዚህ ረገድ የመሪነት ሚና እድትጫወት ይጠይቃል።

https://p.dw.com/p/KTMa
በካይ ጋዞች ይገቱ!

ለአየር ጠባይ መለወጥና ለዓለም የሙቀት መጨመር ምክንያት የሆኑትን በካይ ጋዞች ለመቀነስ በሚል ከዓመታት በፊት በጃፓን ኪዮቶ ላይ በመንግስታት የተፈረመዉ የኪዮቶ ዉል የሚያከትምበት ወቅት እየደረሰ ነዉ። ያንን ያዉም አደገኛ ከባቢ አየር በካይ መሆናቸዉ የሚታወቀዉ አገራት ያልፈረሙበት ዉል በሌላ እንዲተካ የተጀመረዉ ጥረት የኮፐንሃገኑ ጉባኤ ከመድረሱ በፊት እጅግም ተስፋ ሰጪ ምልክት ባለመታየቱ የአካባቢ ተፈጥሮ ተቆርቋሪዎች ዛሬም በየአገሩ ድምፃቸዉን ማሰማት ቀጥለዋል። ሰሚ ጆሮ ካገኘ ጥቅሙ የጋራ ነዉና በኢትዮጵያ ለተጀመረዉ ዘመቻ ፊርማችንን በማኖር በአየር መዛባት ለሚቸገረዉ ወገናችን አጋርነታችንን እናሳይ።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ