1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አልጀዚራ ጋዜጠኛዉ እንዲለቀቅ ጠየቀ

እሑድ፣ ሰኔ 14 2007

ጀርመን ውስጥ በቁጥጥር ስር የዋለውን የአልጃዚራ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ አህመድ ማንሱር በቶሎ እንዲለቀቅ ጣቢያው እና ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማህበር ጠየቁ።

https://p.dw.com/p/1FkWO
Ahmed Mansour
ምስል picture-alliance/dpa/Al-Dschasira

ትናንት ወደ ካታር ዶሀ ለመጓዝ ዝግጅት ላይ የነበረው ታዋቂው ጋዜጠኛ ማንሱር ቅዳሜ ዕለት ነበር በርሊን-ቴግል አይሮፕላን ማረፊያ በጀርመን የድንበር ጠባቂ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው። ግብፅ ውስጥ እብደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 2011 ዓ,ም በተካሄደው አብዮት አህመድ ማንሱር በአንድ ጠበቃ ላይ ለተፈፀመ ድብደባ ተጠያቂ ነህ ተብሎ በጎርጎረሳዉያኑ 2014 ዓ,ም በሌለበት አንድ የግብፅ ፍርድ ቤት የ 15 ዓመት ጽኑ እስራት በይኖበት በዓለም አቀፍ ደረጃ በእስር እንዲያዝ ሲፈለግ ነበር። ማንሱር« አፀያፊ ወቀሳ» ሲል በተደጋጋሚ ከግብፅ የተሰነዘረበትን ወንጀል ማጣጣሉ ይታወቃል። አንዳንዶች የእስር ማዘዣዉ ፖለቲካዊ ምክንያት እንዳለዉ ይናገራሉ። በግብጽ ፍርድ ቤት ከ ጎርጎረሳሺanu 2013 ዓ,ም ጀምሮ የሚፈለገዉ የአልጃዚራ ጋዜጠኛ አህመድ ማንሱር፤ የሙስሊም ወንድማማች ማኅበር አባል መሆኑም ተመልክቶአል። እንደ ጋዜጠኛው ጠበቃ ከሆነ፤ ማንሱር ለጊዜው በጀርመን የፖሊስ ቁጥጥር ስር ይቆያል።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ