1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኅብረተሰቡ የሚሰማዉ ካገኘ የራሱን ድርሻ ይወጣል

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2001

ለአንድ ዓመት ካቀድክ እህል ዝራ፤ ለአስር ዓመታት ካለምክ ዛፍ ትከል፤ ለመቶ ዓመታት ካሰብክ ደግሞ ህዝብን አስተምር የሚለዉ የፈላስፋዉ የኮንፊሺየስ ታዋቂ አባባል ለኢትዮጵያ የደን ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት መሪ መፈክር ነዉ።

https://p.dw.com/p/H9G5
...የአፈሩ ለምነት ያነጋግራል...
...የአፈሩ ለምነት ያነጋግራል...ምስል AP

በዚህ ድርጅት ዉስጥ በአባልነት ተሰባስበዉ የበኩላቸዉን የሚያደርጉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪዎች የተለያየ ሙያ ባለቤቶች ሲሆኑ ኅብረተሰቡ የሚሰማዉ ካገኘ የደን መራቆትን ለመለወጥ የበኩሉን እንደሚያደርግ ያምናሉ። መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተብሎ ህግዊ እዉቅና ያገኘዉ የኢትዮጵያ የደን ልማት በጎ አድራጎት ድርጅት መስራችና ጠንሳሾች በአሜሪካን አገር ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ።