1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኃይል የቀላቀለዉ የሱዳን ተቃዎሞ

ሰኞ፣ ግንቦት 26 2011

ዛሬ ጎረቤት ሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሻርን የተካዉ የሱዳን የሽግግር መንግሥትን ስልጣን እንዲለቅ የሚጠይቀዉ ተቃዉሞ ጠንክሮ ዉሎአል። የሱዳን ጦር ኃይል ለተቃዉሞ በወጡ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ተኩስ በመክፈት ቢያንስ 13 ሰዎች ተገለዋል።

https://p.dw.com/p/3JlsO
Sudan Proteste in Khartum
ምስል Getty Images/AFP/A. Shazly

የሱዳን ጦር ኃይል ለተቃዉሞ በወጡ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ላይ ተኩስ በመክፈት ቢያንስ 13 ሰዎች መግደሉ ተገለፀ። የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንዘገበዉ መዲና ካርቱም ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ዉጥረት ነግሶአል። የሱዳን የሕክምና ማኅበርን ጠቅሶ የጀርመኑ የዜና አገልግሎት (dpa) በበኩሉ አንድ ሕጻንን ጨምሮ 13 ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም  ሌሎች ብዙዎች መቁሰላቸውን ዘግበዋል። ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሰላም ፍትህ እያሉ በተቃዉሞ ጎማ በየአደባባዩ ጎማ ሲያቃጥሉ ታይቶአል። ካርቱም የሚገኘዉ የሱዳን የሰራተኛ ማኅበር ፕሬዚዳንት አልባሽርን ከስልጣን ያስወገደዉ የሱዳኑን ወታደራዊ መንግሥት የመሰረተዉ የሽግግር መንግሥትን በመቃወም ካርቱም እምብርት ላይ ለሳምንታት በመቀመጥ ተቃዉሞአቸዉን በመግለፅ ላይ ያሉትን የተቃዉሞ ሰልፈኞች የሱዳን ወታደሮች በኃይል ለመበተን ሞክረዋል ሲል ተናግሮአል። ኻርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ "የሱዳን የጸጥታ ኃይሎች በተቃዋሚዎች እና ሲቪሎች ላይ የፈጸሙት ጥቃት ስሕተት ሲል ኃላፊነቱ በወታደራዊ የሽግግር መንግሥት እጅ ላይ ነዉ" ሲል እርምጃውን ኮንኗል። የተቃዉሞ አስተባባሪዎች ለሽግግሩ መንግሥት ምንም አይነት ንግግር እንደማይፈልጉ ነገር ግን ሥልጣኑን እንዲለቅ እየወተወቱ ነዉ። የሱዳኑ የሰራተኛ ማኅበር ባለፈዉ ሚያዝያ ወር ጀምሮ የሱዳኑን የሽግግር መንግሥትን በመቃወም ካርቱም ላይ የጀመረዉን የተቃዉሞ ንቅናቄ በመርዳት ላይ መሆኑ ይታወቃል።  

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ