1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ችኩንጉንያ በፍጥነት መሠራጨቱ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 23 2011

ወረርሽኙ በከፍተኛ ፍጥነት ለመሠራጨቱ ምክንያት ነው የተባለውም የክረምቱ ዝናም ማየልና የሚያቁሩ ውሐዎች መብዛት ነው ሲል የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለይ ለዶቼ ቬሌ ዛሬ ተናግሯል። ከወባ በሽታ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ላለው ለዚህ  ወረርሽኝ፣ የመሰል በሽታዎች አስታጋሽ መድሐኒቶች እንጅ ራሱን የቻለ መድሃኒት እንደሌለውም ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/3Oh7e
Stadtansicht von Addis Abeba Hauptstadt von Aethiopien
ምስል Imago/photothek

አሳሳቢው የቺኩንጉንያ ሥርጭት

  
በድሬዳዋ የተከሰተው ችኩንጉንያ የተባለው ወረርሽኝ 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ16 ሽህ ሰዎችን ማጥቃቱን መንግስት አስታወቀ። ወረርሽኙ በከፍተኛ ፍጥነት ለመሠራጨቱ ምክንያት ነው የተባለውም የክረምቱ ዝናም ማየልና የሚያቁሩ ውሐዎች መብዛት ነው ሲል የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በተለይ ለዶቼ ቬሌ DW ዛሬ ተናግሯል። ከወባ በሽታ ጋር ተመሳሳይ ምልክት ላለው ለዚህ  ወረርሽኝ፣የመሰል በሽታዎች አስታጋሽ መድሐኒቶች እንጅ ራሱን የቻለ መድሃኒት እንደሌለውም ተገልጿል። ወረርሽኙ ከዚህ ቀደም በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ተከስቶ የነበር ቢሆንም እስካሁን በበሽታው የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ሪፖርት እንዳልደረሰው ተቋሙ አስታውቋል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ