1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቻርሎት-የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 30 2004

ጉባኤዉ በመጪዉ ጥቅምት ማብቂያ በሚደረገዉ ምርጫ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ዲሞክራቲኩን ፓርቲ ወክለዉ ለድጋሚ ዘመነ-ሥልጣን እንዲወዳደሩ እጩነታቸዉን በይፋ ያፀድቃል።ኦባማ ነገ ስታዲዮም ዉስጥ ሊያደርጉት የነበረዉ ንግግር ግን በአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት አዳራሽ ዉስጥ እንዲደረግ ዛሬ ተወስኗል።

https://p.dw.com/p/1644q
Delegates applaud during the first session of the Democratic National Convention in Charlotte, North REUTERS/Jim Young (UNITED STATES - Tags: POLITICS ELECTIONS)
የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤምስል Reuters

ቻርሎት-ኖርዝ ካሮላይና የተሰየመዉ የዩናይትድ ስቴትስ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ የተቃዋሚዉን የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳት የሚት ሮምኒን መርሕ እያብጠለጠለ፥ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማን ማድነቀ-ማወደሱን ዛሬም ቀጥሏል።ትናንት በተጀመረዉ ጉባኤ ላይ ለሚሳተፉ ወደ ሥድስት ሺሕ ለሚጠጉት መልዕክተኞች በየተራ ንግግር ያደረጉት ፖለቲከኞች ቱጃሩ ፖለቲከኛ ሚት ሮምኒ የሚከተሉት መርሕ ዝቅተኛና መከካከለኛ ገቢ ያለዉን አሜሪካዊ የሚጎዳ ነዉ በማለት አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ የመክፈቻዉ ሥነ-ሥርዓት ኮኮብ ነበሩ።ሚሼል ኦባማ ባደረጉት ንግግር ግን የባለቤታቸዉን ተቀናቃኝ ሚት ሮሚኒን እንደ ሌሎቹ ፖለቲከኞች በስም ጠቅሰዉ ከማዉገዝ መዉቀስ ይልቅ የባሌቤታቸዉን ሥነ-ምግባር እና መርሕ ጠቃሚነት ማጉላቱ ላይ ነበር ያተኮሩት።

«እና እንደ ፕሬዝዳንት ከሁሉም ዓይነት ሰዎች ሁሉንም አይነት ምክር ታገኛለሕ።በስተመጨረሻዉ እንደ ፕሬዝዳት ለመወሰን ግን የመርሕሕ መሠረት የሚሆኑት እሴቶችሕ፥ ራዕይሕና አንተን አንተ ያደረጉት ገጠመኞችሕ ናቸዉ።ሥለዚሕ ባራክ ምጣኔ ሐብታችንን ዳግም ለመገንባት ሲያስብ፥ የሚያስበዉ እንደ አባቴና እንደ አያቱ ያለዉን ሕዝብ ነዉ፥ የሚያስበዉ ጠክሮ ከመስራት የሚገኘዉን ኩራት ነዉ።»

ጉባኤዉ በመጪዉ ጥቅምት ማብቂያ በሚደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ዲሞክራቲኩን ፓርቲ ወክለዉ ለድጋሚ ዘመነ-ሥልጣን እንዲወዳደሩ እጩነታቸዉን በይፋ ያፀድቃል።ኦባማ ነገ-እጩነታቸዉን በመቀበል ስታዲዮም ዉስጥ ሊያደርጉት የነበረዉ ንግግር ግን በአየር ጠባይ ለዉጥ ምክንያት አዳራሽ ዉስጥ እንዲደረግ ዛሬ ተወስኗል።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ