1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግል ከካንሠር ጋር፣

ረቡዕ፣ ግንቦት 1 2004

ኢትዮጵያውያንን በየጊዜው የሚያስጨንቁ፤ ድርቅ፤ ረሃብ፣ የተለያዩ በሽታዎች፣ ሌሎቹም የተፈጥሮና ሰው-ሠራሽ ችግሮች እንዳሉ ሆነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በነቀርሳ በሽታ የሚሠቃዩና ህይወታቸውን የሚያጡት ወገኖች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው

https://p.dw.com/p/14sTR
ምስል picture-alliance/dpa

ኢትዮጵያውያንን በየጊዜው የሚያስጨንቁ፤ ድርቅ፤ ረሃብ፣ የተለያዩ በሽታዎች፣ ሌሎቹም የተፈጥሮና ሰው-ሠራሽ ችግሮች እንዳሉ ሆነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በነቀርሳ በሽታ የሚሠቃዩና ህይወታቸውን የሚያጡት ወገኖች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ነው የሚነገረው። 85 ሚሊዮን ላላት ሀገር ብቸኛው የነቀርሳ መታከሚያ ማዕከል ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነው። በመሆኑም፣ ችግሩን ለመቅረፍ፣ ብሪታንያ ውስጥ በሚኖሩ 5 ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ፍልሚያ ከካንሠር ጋር በኢትዮጵያ  
የተሰኘ የግብረ ሠናይ ድርጅት፤ ከጤና ጥበቃና ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በመተባበር፣ ስለ ካንሠር ትምህርት ይሰጥ ዘንድ ፤ ለነቀርሳ በሽተኞችና ቤተሰቦችም የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት ማዕከል እንዲቋቋም ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲተባበሩ በማሳሰብ ላይ ነው። --

ሐና ደምሴ-

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ