1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክና የአዉሮጳ ሕብረት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 10 2004

በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ ህብረት እና በቱርክ መካከል ኃይለ ቃላት ተጀምረዋል። የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር አገራቸው በአውሮፓ ህብረት አባል ሐገራት ካለው ኢኮኖሚ ጋ ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት እያሳየ እንደሆነ እና የአውሮፓ ህብረት ጥገኛ እንዳልሆነች

https://p.dw.com/p/14fPu
Flags of Turkey, right, and the European Union are seen in front of a mosque in Istanbul, Turkey, in this Tuesday, Oct. 4, 2005 file photo. European leaders look likely to partially suspend membership talks with Turkey this week because of its refusal to trade with or recognize Cyprus. But Cyprus may turn out to be one of the smallest obstacles to Turkey's membership bid. (AP Photo/Osman Orsal, File)
ምስል AP

ሊያሰምሩበት ይወዳሉ። ወደ ቱርክ ተጉዘው በቦስፓሩስ ድልድይ ላይ ወደ ምስራቅ ሲጓዙ በሌላኛው መዳረሻ በትልቁ አንድ ምልዕክት ይነበባል። «እንኳን ወደ እስያ በደህና መጡ» የሚል። ይህ ከአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች ተርታ ለመሰለፍ ለምትሞክረው ቱርክ የችግሩ አንድ ነጥብ ነው። ብዙ ጥያቄዎች ባለፉት አመታት ተነስተዋል። 98 ከመቶው የእስልምና እምነት ተከታይ በሆነናት አገር እና በመልክዓ ምድር አቀሟመጧ ከአውሮፓ ይበልጥ በእስያ አህጉር የምትገኘው ቱርክ በዕርግጥ የአውሮፓ ህብረት አባል መሆን ትችል ይሆን የሚል?! ቢያንስ ለጥያቄው መልሱን ቱርክ ካገኘች ውላ አድራለች። እኢአ ሚያዚያ 14 1987 ዓ ም ቱርክ በዛን ጊዜ ከአውሮፓ ህብረት በፊት ለነበረው የአውሮፓ ማህበረሰብ ጥያቄዋን ታቀርባለች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያለፈው ቅዳሜ 25 ዓመታት ተቆጠሩ። እስካሁን እንብዛም ለቱርክ አርኪ ውጤት ላይ አልተደረሰም። የተደረሰበት ነገር ቢኖር እኢአ 1999 ዓ ም የአባል እጩነት እና ከ2005 ጀምሮ የአባልነት ጥያቄ ድርድሩ በይፋ መጀመሩ ነው። በሌላ በኩል ግን ከቱርክ በኋላ የአባልነት ጥያቄ ያቀረቡ እና በኢኮኖሚያቸው እንደ ቱርክ ያልበለፀጉ አገራት የአውሮፓ ህብረት አባል ሆነዋል።

አሁን እንደ ጀርመን እና ፈረንሳይ ባሉ ሐገራት በስልጣን ላይ ያሉ መንግስታት የቱርክ አባልነት ጥያቄን ተቀባይነት እንዳያገኝ ይዘዋል። ጀርመን ውስጥ በስልጣን ላይ ያለው የክርስትያን ዲሞክራቲክ ህብረት ፓርቲ (CDU) የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት የህዝብ እንደራሴ ኤልማር ብሮክ እንደሚሉት፤ ቱርክ የአውሮፓ ህብረት ሙሉ አባል ብትሆን ራስዋ ቱርክም የአውሮፓ ህብረትም ይጎዳሉ። «እንደሚመስለኝ የአውሮፓ ህብረት አሁን ቱርክን የሚያክል ትልቅ ሀገር ተቀብሎ መቋቋም የሚችል አይመስለኝም። በዚህም የተነሳ በመጀመሪያ ከሸንገል ጋ የንግድ ትስስር እንዳላት እንደ ኖርዌይ አይነት ተቀባይነት ብታገኝ፤ ይህ በጣም ትልቅ እና የሁለቱንም ፍላጎቶች የሚያረካ ይመስለኛል።»

ግጭት ከሚያስነሱት ጥያቄዎች ጥቂቱ፤ የእምነት ነፃነት፣ የሴቶች የፆታ እኩልነት እና የቆጵሮስ ጉዳይ ነው። በተለይ በዚች የመካከለኛው ምስራቅ የምትገኝ ደሴት ላይ የሚደረገው ግጭት የቱርክን የአባልነት ጥያቄ ከ2006 ዓ ም ጀምሮ እንዲጓተት አድርጓል። በእንደዚህ ምክንያቶች የተነሳ በከፊል የአውሮፓ ህብረት አባላት፤ «ይህቺ ፍፁም በመልከዓ ምድር አቀማመጧም ይሁን በባህሏ አውሮፓን የማትወክል አገር ለአባል አገራቱ ችግር ፈጣሪ ልትሆን ትችላለች» በማለት ይቃወማሉ።
በሌላ በኩል የቱርክ ተማጋቾች ይቺ አገር ለአውሮፓ ያላትን የጎላ ትርጉም እና የሚኖራትን ስልታዊ ጠቀሜታ ይገልፃሉ። በአለም አቀፍ ደረጃ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ቀንሷል። ስለሆነም የአውሮፓ ህብረትን በማስፋፋት ብቻ ነው አውሮፓ ኃይል ሊኖራት እና ተፅዕኖ ማሳደር የምትችለው። ሌላኛው ነጥብ፤ ቱርክ አባል ሀገር ከሆነች፤ በአውሮፓ ለሚኖሩት ቱርኮችም ሆነ ለሌሎች ሙስሊም አገራት አውሮፓ አንድ ምሳሌ የምትጠራ ትሆናለች የሚል ነው። በዚህም የተነሳ አውሮፓ በምዕራቡ እና በሙስሊሙ አለም የተነሳውን ውጥረት ትቀንሳለች። የአውሮፓ ህብረት የማስፋፋት ኮሚሽነር እስቴፋን ፉይለ፤ በቱርክ ላይ ሙሉ እምነት አላቸው።
«ወሳኝ አገር ነች። በኃይል አቅራቡቱ መስክም ቢሆን ወሳኝ አገር ነች። ለዛ ስንል ነው ከቱርክ ጋ የምንተሳሰረው። አዎ ለዛ ስንል ነው እጅግ በጣም ከቱርክ ጋ ስለ መቀላቀል ልንወያይ የምንሻው። ምክንያቱም ይህ ቱርክን ዘመናዊ ለማድረግ ያለን መሳሪያ ነው።»

ይሁንና በአሁኑ ሰዓት በአውሮፓ ህብረት እና በቱርክ መካከል ኃይለ ቃላት ተጀምረዋል። የቱርክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሬቼፕ-ታይፕ-ኤርዶሃን አገራቸው በአውሮፓ ህብረት አባል ሐገራት ካለው ኢኮኖሚ ጋ ሲነፃፀር ከፍተኛ እድገት እያሳየ እንደሆነ እና የግድ የአውሮፓ ህብረት ጥገኛ እንዳልሆነች ሊያሰምሩበት ይወዳሉ። ሌሎች እንደ ግሪክ ያሉ አገራት እየከሰሩ ገፅታቸው ሲበላሽ ቱርክ ጠንካራ በራስ መተማመንን ታሳያለች። ይበልጥ በቱርክ የአውሮፓ ህብረት የአባልነት ጥያቄ ላይ የተነሳው ክርክር እንዳይከር የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ ለዘብ ያለውን ቃል ነው የመረጡት።
«ወደ አውሮፓ ህብረት የመቀላቀሉን ጥያቄ በግልፅ የምቃወም አይደለሁም። ዛሬ ስላልተነሱ ጥያቄዎች ሳይሆን ቱርክ በአግባቡ እንድትያዝ በክብር እንድትታይ እና የተጀመረውን ሂደት መጨረሻውን ባናውቅም አውሮፓ ቀጠሮ የያዘችበትን እንደምታከብር ቱርክም እንድታውቅ ያስፈልጋል። ይህንን ነው የአውሮፓ ህብረት እና የቱርክ መንግስታት የተስማሙት።»

ሀቁን አድበስብሰው ላለማለፍ የደፈሩት የጀርመን አረንጓዴው ፓርት እንደራሴ ራይንሀርድ ቡቲኮፈር ናቸው። እንደሳቸው፤ ውይይቱ የምጣኔ ሀብታዊ እና የፖለቲካዊ ብቻ አይደለም።
« ስለ አውሮፓ ማንነት ያለን አመለካከት -አውሮፓ የክርስትያን ክለብ ከሆነች ቱርክ ውጪ ትቀራለች። አይ አውሮፓ የአውሮፓውያን የእስልምና ታሪክ በቁም ነገር ትመለከታለች ከተባለ ቱርክ ያመለከተችውን ጥያቄ በአግባቡ መመልከት ያስፈልጋል።»

ይሁንና የአውሮፓ ምክር ቤት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለቱርክ አባልነት የቆሙ ጥቂት ናቸው። የጀርመን መራሒተ መንግስት አንጌላ ሜርክልም ቢሆኑ ቱርክን በተመለከተ ሀሳብ ከመስጠት ተቆጥበዋል። ስለሆነው እንደ ካዴር ሴፊኒች ላሉ ፤ቱርክ የአውሮፓ ህብረት አባል እንድትሆን የሚከራከሩ አግባቢዎች ብዙ ስራ ይጠብቃቸዋል።
« በቱርክ ዲሞክራሲን ወይም እምነትን ከሀገር ለይቶ በመልከትን አኳያ በተመለከተ ችግር አለ። ይሁን እና ቱርክ ለሌሎች አካባቢዎች ምሳሌ የምትሆን ሀገር ናት።»

ስለሆነም ቱርክ የአውሮፓ ህብረትን ብትቀላቀል ለቀጣይ ዲምክራሲያዊ አካሄድ እና ለአገሪቷ እድገት ወሳኝ ነው ይላሉ- ካዴር ሴፊኒች። እንዳም ሆኖ ድርድሩ ረጅም ጊዜ ስለፈጀ በአሁኑ ሰዓት በርካታ ቱርኮች ተናደዋል።
« ይህ ወደፊት መራመድ እና መቋጫ ያጣው የድርድር ምዕራፍ የአውሮፓ ህብረት ገፅታን ጓድቷል። ይህ በቱርኮች አመለካከት የአውሮፓን ህብረት ተአማኒነትን ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጓል። በርካታ ቱርኮች ተፈላጊነት እንደሌላቸው ነው የተሰማቸው።»

ሴፊኒች የሚወኩሉት ትልቁ የቱርክ ተቃዋሚ ፓርቲ መምህፃሩ CHP ብቻ ሳይሆን ይበልጡ የቱርክ ህዝብ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉ አሟልተው የአውሮፓ ህብረትን መቀላቀል ነው የሚፈልጉት። አንዳንድ የአውሮፓ ፖለቲከኞች አገራቸው የአውሮፓ ህብረትን እንዳትቀላቀል በአጠቃላይ ሲያወግዙ አይገባኝም ይላሉ ሴፊኒች! « የቱርክን የድርድር ምዕራፍ በመዝጋት!የቱርክን ዕቅድ የሚዘጉ አይመስለኝም። የሚዘጉት የአውሮፓን የወደፊት እጣ እና የአውሮፓ ዜጋን ፍላጎት ጭምር ነው።»

ሴፊኒች ሁለቱንም አካል አግባባለሁ ብለው ያምናሉ። መጨረሻውም ጥሩ ነው የሚሆነው።
« ሁላችንም የተሻለች አውሮፓ ታስፈልገናለች። እዚህ ያለነው እንደ አውሮፓዊ በዚህ ክርክር ላይ የበኩላችንን ድርሻ ማበርከት እና የአውሮፓን ዲሞክራሲ ለማጠናከር ነው።
ቱርክ የአውሮፓ ህብረት አባል ትሆናለች። »

የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ ይህ እውን እስኪሆን -ካዴር ሴፊኒች ትግላቸውን ይቀጥላሉ። የጀርመኑ የቀድሞ መራይተ መንግስት ጌርሃርድ ሽሮደር እንደሚያምኑት ከሆነ፤ ቱርክ በ20 አመታት ውስጥ በኢኮኖሚ እድገት ከአውሮፓ ሕብረት የአራት ወይም አምስተኛነትን ስፍራ ትይዛለች። ያም ሆኖ የቱርክ የአውሮፓ ህብረት አባል መሆን ለጊዜው በቃላት እና በምኞት ብቻ ይቆያል።

Turkey's Prime Minister Recep Tayyip Erdogan, right, and German Chancellor Gerhard Schroeder listen to their nations' anthems during a welcoming ceremony for Schroeder in Ankara on Monday, Feb. 23, 2004. (AP Photo/Burhan Ozbilici)
ኤርዶሃን እና ሽሮደርምስል AP
Turkey's Prime Minister Recep Tayyip Erdogan, right, and German Foreign Minister Guido Westerwelle pose for cameras before their meeting in Istanbul, Turkey, Thursday, Oct. 13, 2011. Foto: Mustafa Ozer/Pool/dapd
ጊዶ ቬስተርቬለ እና ኤርዶሃንምስል dapd
Der Blick auf die Bosporusbrücke in Istanbul, die Europa mit Asien verbindet, aufgenommen am Dienstag (05.05.2009). Bis Ende Mai finden in Istanbul Dreharbeiten für den Film "Mordkommission Istanbul - Mord am Bosporus" statt. Foto: Ulrich Perrey +++(c) dpa - Report+++ pixel
ኢስታንቡልምስል picture-alliance/dpa


ልደት አበበ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ