1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተከሳሹ አጭበርባሪ ካገር ወጣ

ሐሙስ፣ መስከረም 15 2007

ተበዳዮቹ እንደሚሉት ተጠርጣሪዉ ክስ ተመሥርቶበት ከሐገር እንዳይወጣ በፍርድ ቤት ቢታገድም በኬንያ አቋርጦ ዱባይ መግባት አልተሳነዉም::

https://p.dw.com/p/1DL0T
ምስል Getty Images

ሠዎችን ወደ አዉሮጳና አሜሪካ እልካችኋላሁ በማለት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ያጋበሰ አንድ ኢትዮጵያዊ ከሐገር መዉጣቱ ተነገረ።ሳሙኤል ቦጋለ የተባለዉ ግለሠብ ወደ ዉጪ እልካችኋላሁ በማለት ከበርካታ ሰዎች ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ መዝረፉን ተበዳዮች አስታዉቀዋል።ተበዳዮቹ እንደሚሉት ተጠርጣሪዉ ክስ ተመሥርቶበት ከሐገር እንዳይወጣ በፍርድ ቤት ቢታገድም በኬንያ አቋርጦ ዱባይ መግባት አልተሳነዉም።የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች «ወንጀለኛ» የሚሏቸዉን ሰዎች ዉጪ ሐገር ድረስ እየዘመቱ ሲይዙ የፍርድ ቤት ብይንን ያላስከበሩበት ምክንያት እያነጋገረ ነዉ።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ