1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞ በኢትዮጵያ ቆንስላ ላይ

ዓርብ፣ መጋቢት 28 2004

በሊባኖስ ቤይሩት ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ፣ ህይወቷን አጠፋች የተባለችው የዓለም ደቻሳ ሞት ከተነገረበት ማግስት አንስቶ ቤይሩት ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በመሄድ ቁጣቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን የጂዳው ወኪላችን ነበዩ ሲራክ ዘግቧል ።

https://p.dw.com/p/14Z5h
ቤይሩት ከተማምስል AP


በሊባኖስ ቤይሩት ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ፣ ህይወቷን አጠፋች የተባለችው የዓለም ደቻሳ ሞት ከተነገረበት ማግስት አንስቶ ቤይሩት ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ በመሄድ ቁጣቸውን ሲያሰሙ መቆየታቸውን የጂዳው ወኪላችን ነበዩ ሲራክ ዘግቧል ። ዓለም ቆንስላው በር ላይ ስተሰቃይ በነበረበት ወቅት የሚደርስላት ማጣቷ ያስቆጫቸው እነዚሁ ኢትዮጵያውያን የቆንስላው ባለሥልጣናት መብታችንን ያስጠብቁ አለያም ለቀው ይውጡ በማለት በተለያዩ መንገዶች ተቃወሞአቸውን እየገለጹ ነው ። በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል በበኩላቸው ዜጎች ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑንና ጉዳዩንም የሊባኖስ መንግሥት እየተመለከተው መሆኑን ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።

ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሥ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ