1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃዉሞ የጋረደዉ የትራምፕ የብሪታንያ ጉብኝት

ሰኞ፣ ግንቦት 26 2011

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሦስት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ብሪታንያ መዲና ለንደን ገቡ። ትራምፕ በጉብኝታቸዉ መጀመርያ ከንግስት ኤልዛቤጥ ጋር ተገናኝተዋል። ንግስት ኤልሳቤጥ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ  የምሳ ግብዣና ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸዉም ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3Jlkk
Großbritannien London Besuch Donald Trump
ምስል DW/B. Riegert

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሦስት ቀን ይፋዊ ጉብኝት ብሪታንያ መዲና ለንደን ገቡ። ትራምፕ በጉብኝታቸዉ መጀመርያ ከንግስት ኤልዛቤጥ ጋር ተገናኝተዋል። ንግስት ኤልሳቤጥ ለፕሬዚዳንት ትራምፕ  የምሳ ግብዣና ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸዉም ታዉቋል። ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸዉን በቅርብ ቀናት ዉስጥ ከሚለቁት ከብሪታንያዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ጋር ደግሞ ነገ ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ትራምፕ በጉብኝታቸዉ መጀመርያ በትዊተር መልክታቸዉ ትዉልደ ፓኪስታን የሆኑትን የለንደኑን ከንቲባ ሳዲቅ ካንን መወረፋቸዉ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶባቸዋል። ትራምፕ ከፓኪስታን የመጡ ወላጆች ያሏቸዉና ለንደን የተወለዱት የለንደኑ ከንቲባ ዛዲግ ካንን  «እንደ ድንጋይ ቀዝቃዛና ተሸናፊ» ብለዉ ትዊተር ላይ በመፃፋቸዉ ሰዉየዉ ዘረኛ፤ መጤ ጠል ናቸዉ የሚል ወቀሳ ተነስቶባቸዋል። ትራምፕን በመቃወም ለንደን ከተማ ላይ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።  

 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ