1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተለያይተው የቆዩት የህወሓት አመራሮች በጋራ መድረክ  

ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2011

በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን የካቲት 11 በዓል በጋራ አከበሩ፡፡ በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡

https://p.dw.com/p/3Dg2s
Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

የካቲት 11 የሕወሃት በዓል ብቻ አይደለም

በፖለቲካዊ ምክንያት ለዓመታት ተለያይተው የቆዩት የህወሓት ነባር አመራሮች ትላንት በመቐለ ተገናኝተው 44ኛውን የካቲት 11 በዓል በጋራ አከበሩ፡፡ በመድረኩ ለሁሉም የህወሓት ታጋዮችና የቀድሞ አመራሮች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 1993 ዓ.ም ህወሓት ካጋጠመው ክፍፍል በኋላ ነባር የሚባሉት የድርጅቱ አመራሮች ፖርቲው ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ በአንድ መድረክ ተገናኝተው ትግል የጀመሩበት 44ኛውን ዓመት የካቲት 11 አክብረዋል፡፡ አስተያየታቸውን የሰጡን የቀድሞ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ዓረና ትግራይ የተባለ ፖርቲ መስርተው እየተንቀሳቀሱ ያሉት አቶ ገብሩ አስራት "የካቲት 11 የአንድ ድርጅት በዓል ተደርጎ እየተከበረ መቆየቱ ተገቢ አልነበረም" ብለዋል፡፡ የቀድሞ ታጋይ፣ ከትግል በኋላ የመከላከያ ሚኒስተር የነበሩት እንዲሁም ከክፍፍሉ በኋላ ለዓመታት ታስረው የተፈቱት አቶ ስየ አብረሃ በበኩላቸው "ብዙ መቆሳሰል ቢያልፍም የጋራ ታሪክ አለን" በማለት በአሉ ከቀድሞ ጓዶቻቸው ጋር ማክበራቸው ጥሩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ የወቅቱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላት እንዲሁም የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የመድረኩ አዘጋጅ የትግራይ ክልል ንግድና ዘርፍ ማሕበራት ምክርቤት መሆኑ ተገልጿል፡፡

 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ሸዋዬ ለገሠ