1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብአዴን እና የተራዘመ ስብሰባው

ዓርብ፣ የካቲት 16 2010

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን) የመዓከላዊ ኮሚቴ ውይይቱን ትናንት ማጠናቀቁን በድርጅቱ ማኅበራዊ መገናኛ አውታሮቹ ዛሬ ዐሳውቋል።

https://p.dw.com/p/2tEc2
Äthiopien Ausnahmezustand
ምስል James Jeffrey

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ብአዴን) የመዓከላዊ ኮሚቴ ውይይቱን ትናንት ማጠናቀቁን በድርጅቱ ማኅበራዊ መገናኛ አውታሮቹ ዛሬ ዐሳውቋል። ብአዴን ከጥር 12 ጀምሮ በየመሀከል እያቋረጠ ሲያከናውን የቆየውን ስብሰባውን ሙሉ መግለጫ ዛሬ እዛው የማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ላይ ከሰአታት በኋላ እንደሚያቀርብ ቢገልጥም ስርጭታችን እስከሚተላለፍበት ድረስ ላሉት ስምንት ሰአታት መግለጫውን አላወጣውም። ብአዴን በቅርብ ጊዜ የነበረው በፍጥነት መረጃን ይፋ የማድረግ አዝማሚያ ምሥጢራዊ  የኾነበት ምክንያት ምንድን ነው? በድርጅቱ መካከከል በአባላቱ መካከል ያለው ግንኙነትስ ምን ይመስላል? አቶ ውብሸት ሙላትን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬያቸው ነበር። ሙሉ ቃለ መጠይቁ ከታች የድምጽ ማገናኛ ውስጥ ይገኛል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሠ