1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጉባኤዉ እስከ ነሐሴ ማብቂያ ይደረጋል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2010

የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እንደሚሉት ጉባኤዉ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ ዉጪም ሐገር ዉስጥም ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የሲቢክ ማሕበራት እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ተቋማት የሚካፈሉበት ነዉ

https://p.dw.com/p/319lU
Äthiopien | AEUP Vorsitzender Dr. Bezabeh Demisse
ምስል Getachew Tedla HG

(Beri.AA) Five opposition parties call for national dialogue - MP3-Stereo

ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔራዊ የመግባባት እና የእርቅ ጉባኤ ለማድረግ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ እየጣሩ መሆኑን አስታወቁ።የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እንደሚሉት ጉባኤዉ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ ዉጪም ሐገር ዉስጥም ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የሲቢክ ማሕበራት እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ተቋማት የሚካፈሉበት ነዉ።ለጉባኤዉ በሚደረገዉ ዝግጅት እና በራሱ በጉባኤዉ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ በሙሉ እንዲሳተፉ የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥሪ አድርገዋል።ተወካዮቹ እንደሚሉት ጉባኤዉን እስከ መጪዉ ነሐሴ ወር ድረስ ይደረጋል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ