1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሄራዊ ቡድኑ ይመሰገናል

ቅዳሜ፣ ጥር 18 2005

በትናንት ምሽት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና በቡርኪና ፍሶ የእግር ኳስ ቡድን መካከል በተደረገዉ ጨዋታ ዉጤት፤ በርካታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪዎችን አሳዝኖአል።

https://p.dw.com/p/17S67
ምስል Himanot Tiruneh

ተጫዋች አዳነ ግርማና እስራት መገርሳ በደረሰባቸዉ ጉዳት ከጨዋታዉ ዉጭ ባይሆኑ ኖሮ ምናልባትም ይህ ዉጤት ባልተከሰተ ነበር፤ ሲሉ በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች አስተያየታቸዉን ይሰጣሉ። አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ በበኩላቸዉ በድክመታችን ዋጋ ከፍለናል ማለታቸዉ ተመልክቶአል። በደቡብ አፍሪቃ እንዲሁም በዓለም ዙርያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎች የጨዋታዉ ዉጤት ቢያሳዝነንም ከ 31 ዓመታት በኋላ በአፍሪቃ ደረጃ እንድንጋጠም እና ስማችን እንዲጠራ ላበቁን ለብሄራዊ ቡድን አባላቶቻችን እና ለአሰልጣኙ ከፍ ያለ ምስጋና ሊቀርብላቸዉና ልናወድሳቸዉ ይገባል፤ በማለት በሞራል ከብሄራዊ ቡድን ጎን እንደሚቆሙ በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛዎች አስተያየታቸዉን እየገለፁ ነዉ። ሃይማኖት ጥሩነህ የትናንቱን ጨዋታ በስቴድዮም ተከታትላ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራልናለች።

ሃይማኖት ጥሩነህ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ