1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ባህላዊ ህክምና በኢትዮጵያ

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005

ባህላዊውን ህክምናን ከዘመናዊ ህክምና ጋር ማቀናጀቱ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ። የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሓኒት አዋቂዎች ማህበር ፣በአሁኑ ጊዜ ትክክለኛውንና ሃሰተኛውን የባህል መድኃኒት አዋቂ መለየቱ ደግሞ ሌላው አሰቸጋሪ ጉዳይ መሆኑም አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/188vH
ምስል picture-alliance / africamediaonline

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዘመናዊ መድኃኒት በበለጠ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውለው የባህል መድሐኒት  በጥናትና ምርምር ሊደገፍ እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች አሳሰቡ ። የባህል መድሐኒት አዋቂዎች ተመራማሪዎች እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች  አዲስ አበባ ውስጥ ባካሄዱት አውደ ጥናት እንደተነገረው ባህላዊውን ህክምናን  ከዘመናዊ ህክምና ጋር ማቀናጀቱ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ እንደቀጠለ ነው ።  የኢትዮጵያ ባህላዊ መድሓኒት አዋቂዎች ማህበር  ፣በአሁኑ ጊዜ  ትክክለኛውንና ሃሰተኛውን የባህል መድኃኒት አዋቂ መለየቱ ደግሞ ሌላው አሰቸጋሪ ጉዳይ መሆኑም አስታውቋል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ