1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአውሮጳ ህብረት የአንጌላ ሜርክል ሚና  

ማክሰኞ፣ ጥር 1 2010

ጀርመን የአውሮጳ ምሰሶ በመሆን ህብረቱ በልዩነቶች መካከልም ቢሆን አንድነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ከፍተኛውን ሚና ስትጫወት ቆይታለች። የኤኮኖሚ ኃያልነቷ እና ትልቅነቷ ብቻ ሳይሆን ከሌላዋ ትልቅ ሀገር ፈረንሳይ ጋር ተግባብታ መስራቷ ለህብረቱ መጠናከር በእጅጉ ረድቷል።

https://p.dw.com/p/2qZEe
Angela Merkel EU Flaggen Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/AP Photo/O.Matthys

አንጌላ ሜርክል

በአውሮጳ ህብረት የጀርመን እና የፈረንሳይ ልዩ ትብብር እና መግባባት አንዳንዶች እንደሚሉት ምናልባት ብሪታንያን ከህብረቱ እንድትወጣ ገፋፍቷት ካልሆነ በስተቀር ህብረቱ አሁን ወዳለበት ደረጃ እንዲደርስ ግን ወሳኝ ሚና ነበረው፣ አሁንም አለው። በአውሮጳ ህብረት ውስጥ ጀርመን ለምትጫወትው ሚና ደግሞ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል።

ጀርመንን ላለፉት 12 ዓመታት የመሩት አንጌላ ሜርክል ህብረቱን በሚፈታተኑት ችግሮች ዙርያ የጋራ የመፍትሔ ሀሳቦችን በማፍለቅ እና አባል ሀገራት በአንድነት እንዲቆሙ በማድረግ በኩል ብቃት ያሳዩ መሪ መሆናቸው ይጠቀሳል። ባለፈው መስከረም ወር በተደረገው ምርጫ ሜርክል እና ፓርቲያቸው አሸናፊ ሆነው ጀርመንን ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለመምራት የሚያስችላቸውን መንግሥት ለመመሥረት ጥረት እያደረጉ ነው። ሆኖም ግን የዘንድሮው ምርጫ ውጤት ሜርልን በስልጣን ሊያቆይ የሚችል ከመሆን ባለፈ፣ በተለይ በአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶች ላይ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሆነው ለመቀጠል እንደማይሆን የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ