1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በፓሪስ ግማሽ ማራቶን አሸናፊ ዲባቤ ኩማ

እሑድ፣ የካቲት 27 2008

በፓሪስ ግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር በሴቶች ፉክክር ኢትዮጵያ አሸናፊ ኾነች። ኬንያ በወንዶቹ ቀንቷታል። በሴቶች ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ ዲባቤ ኩማ አንደኛ የወጣችው 1 ሰአት ከ9 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ በመሮጥ ኬንያዊቷ ፒዮሊኔ ዋንጂኩን በ31 ሰከንዶች ቀድማታለች።

https://p.dw.com/p/1I8EG
Frankreich Cop21 Klimagipfel in Paris - Protest Greenpeace
ምስል Reuters/Greenpeace

ፈረንሳዊቷ ክሪስቴሌ ዱናኒ ከኬንያዊቷ በስድስት ሠከንድ ዘግይታ እግር በእርግ በመከተል ሦስተኛ ወጥታለች። በወንዶች የግማሽ ማራቶን ሽቅድምድም አሸናፊ የኾነው ኬንያዊው ሲፕሪየን ኮቱት የገባበት ሰአት 1 ሰአት ከ1 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ ነው። ሌላኛው ኬኒያዊ አሞስ ኪፕሩቶ በሰባት ሰከንድ ተበልጦ ሁለተኛ መውጣት ችሏል። ኢትዮጵያዊው አዝመራው መንግሥቱ በ13 ሰከንዶች ተቀድሞ ሶስተኛ ሆኗል። አራተኛ እና አምስተኛም የወጡት ኬንያውያን ናቸው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ