1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን አንድ የኒዎ ናዚዎች ቡድን ላይ የጀመረዉ ምርመራ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005

እ አ አ በ 2000 እና በ 2007 ዓም መካከል 10 ሰዎችን ገድሏል በተባለው በጀርመን በህቡዕ በሚንቀሳቀሰው የኒዎ ናዚዎች ቡድን አባል በሆነችው ቤአት ሼፐ እና በሌሎች አራት ተባባሪዎችዋ ላይ የተመሠረተውን ክስ ምርመራ ዛሪ በደቡባዊ ጀርመን በሙኒክ ላዕላይ ፍርድ ቤት ጀምሮአል።

https://p.dw.com/p/18TBi
FREI FÜR SOCIAL MEDIA Beate Zschaepe (C), a member of the neo-Nazi group National Socialist Underground (NSU) stands in the court before the start of her trial in Munich May 6, 2013. The surviving member of NSU blamed for a series of racist murders that scandalised Germany and shamed its authorities goes on trial on Monday in one of the most anticipated court cases in recent German history. The trial in Munich will focus on 38-year-old Zschaepe, who is charged with complicity in the murder of eight Turks, a Greek and a policewoman between 2000-2007, as well as two bombings in immigrant areas of Cologne, and 15 bank robberies. REUTERS/Michael Dalder (GERMANY - Tags: POLITICS CRIME LAW)
ምስል Reuters/Michael Dalder

የዛሪ ሁለት ዓመት መንገድ ዳር የሆነ ነገር ተቃጥሎ አመድ ለብሶ የታየዉ መለስተኛ አዉቶቡስ ዉስጥ ፖሊስ የሁለት ወጣቶች ሪሳ በማግኘቱ ነበር  ተጠርጣሪዎቹ፤  በድንገት የተገኙት እና የተያዙት ። ከጥቂት ሰአታት በፊት በዚያኑ ቀን በአካባቢዉ በሚገኝ አንድ ባንክ 70 ሺ ይሮ ሲዘረፍ  ሁለት የብስክሌት አሽከርካሪዎች እንደነበሩ የአይን ምስክሮች ገልጸዋል።

እጅግ አክራሪ የሆነው በህቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረው የአፍላ ናዚዎች እንቅሥቃሴ፤ በተለያዩ ጊዜያት 9 ቱርካውያንናና አንድ ግሪካዊ እንዲሁም አንዲት ጀርመናዊት ፖሊስ መግደሉ ታውቋል። ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረበችው ዋና ተከሳሽ፤ ፤ የዚህ ሁሉ ግድያ ዋና ግብረ- አበር ተብላ የተጠረጠረችው  ቤአተ ቼፐ የተባለችው ናት። ዑቨ ሙንድሎስና ዑቨ Böhnhardt  የተባሉት የዚህ የህቡዕ ድርጅት መሥራቾች፤ እንደተነቃባቸው ህይወታቸውን  በራሳቸው እጅ ማጥፋታቸው ነው የተነገረው። ዋናው ጥያቄ እነዚህ ወገኖች የመንግሥት ፀጥታ አስከባሪ ኃይሎች ሳያውቁባቸው እንዴት 10 ዓመት ሙሉ  አቅድ እያወጡ የሰው ነፍስ አጠፉ ? የሚለው ነው። የፍርዱ ምርመራና ሂደት  ሰፊ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቷል ፣ በተለይ በቱርክ!በዛ ያሉ የቱርክ የህዝብ እንደራሴዎች   ም/ቤት አባላትም ፣ የምርመራውን ሂደት ለመከታተል ወደ ሙዑሸን ተጉዘዋል። ዝርዝሩን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል አጠናቅሮታል።

Defendant E. covers his face before the trial of the neo-Nazi group National Socialist Underground (NSU) members in Munich May 6, 2013. The surviving member of NSU blamed for a series of racist murders that scandalised Germany and shamed its authorities goes on trial on Monday in one of the most anticipated court cases in recent German history. The trial in Munich will focus on 38-year-old Beate Zschaepe, who is charged with complicity in the murder of eight Turks, a Greek and a policewoman between 2000-2007, as well as two bombings in immigrant areas of Cologne, and 15 bank robberies. REUTERS/Michael Dalder (GERMANY - Tags: POLITICS CRIME LAW)
ምስል Reuters/Michael Dalder

ይልማ ሃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ