1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በድሬዳዋ ዕጩ ያስመዘገበ ተፎካካሪ ፓርቲ የለም

ቅዳሜ፣ የካቲት 13 2013

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በመጪው ሰኔ በሚካሄደው የፌደራል የህዝብ እንደራሴዎች እና የከተማ ምክር ቤት  ምርጫ እስካሁን ዕጩ ያስመዘገበ ተፎካካሪ ፓርቲ አለመኖሩን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ በገጠር የሚገኙ የምርጫ ማስፈፀሚያ ጣቢያዎችን ስራ ለማከናወን የተሽከርካሪ እጥረት ማጋጠሙን ጽ/ቤቱ አስታውቋል፡፡

https://p.dw.com/p/3pdQx
Äthiopien Stadansicht Dire Dawa
ምስል DW/M. Teklu

በድሬዳዋ ዕጩ ያስመዘገበ ተፎካካሪ ፓርቲ አለመኖሩ

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በመጪው ሰኔ በሚካሄደው የፌደራል የህዝብ እንደራሴዎች እና የከተማ ምክር ቤት  ምርጫ እስካሁን ዕጩ ያስመዘገበ ተፎካካሪ ፓርቲ አለመኖሩን በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡ የምርጫ ሂደቱን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ በገጠር የሚገኙ የምርጫ ማስፈፀሚያ ጣቢያዎችን ስራ ለማከናወን የተሽከርካሪ እጥረት ማጋጠሙን በመጥቀስ የከተማ መስተዳድሩ ለጽ/ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡በድሬደዋ ከተማ አስተዳድር በከተማ እና በገጠር አራት አራት የምርጫ ማስፈፀሚያ ጣቢያዎች መኖራቸውን የተናገሩት በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዛይድ ያሲን በተሽከርካሪ እጥረት ሳቢያ በሶስት የገጠር ጣቢያዎች ለሁለት ቀናት ስራ መስተጓጎሉን በመጥቀስ ፤ ቦርዱ ባወጣው የድርጊት መርሃ ግብር መሰረት ስራውን ማከናወን እንዲችል የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡በከተማው ሙሉ በሙሉ ስራቸውን በጀመሩት ጣቢያዎች እስካሁን የአንድ ፓርቲ ምዝገባ መካሄዱን የተናገሩት አቶ ዛይድ እስካሁን አንድም ተፎካካሪ ፓርቲ አለመምጣቱን ጠቅሰዋል፡፡በያዝነው ዓመት በክልል ፓርቲነት ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፓርቲዎች መኖራቸውን በመጥቀስ አሁን በመስተዳድሩ በሚካሄደው ምርጫ ለውድድር የቀረበ ክልላዊ ፓርቲ አለመኖሩን አስረድተዋል፡፡ህብረተሰቡ አሁን እየተካሄደ በሚገኘው የዕጩዎች ምዝገባም ሆነ ቀጣይ እንቅስቃሴ በቅርበት እንዲከታተል ጥሪ አቅርበዋል፡፡ቦርዱ ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ የሚካሄድበት ጊዜ ቢጀመርም እስካሁን ቅስቅሳ ለማድረግ ጥያቄ ያቀረበ ፓርቲ አለመኖሩን ለማወቅ ተችሏል፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ