1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ ክልል የተቀሰቀሰ ግጭት የ5ሰዎች ህይወት አጠፋ

ሰኞ፣ ጥር 2 2003

በደቡብ ኢትዮጵያ ግጭት ተቀስቅሶ አምስት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተገለፀ። የግጭቱ መንስኤ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ነዋሪዎች ዘንድ የይገባኛል አተካሮ ያስነሳችው ኤዶ የተባለችው ቀበሌ መሆኗም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/QpaU
ምስል AP

ግጭቱ በእርግጥ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ አከባቢ ነው የተቀሰቀሰው። የሲዳማንና የጉጂ ብሄረሰቦችን ሲያነታርኩ የነበሩ 13 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ በ2000 ዓም ከተካሄደባቸው በኋላ ግጭቱ በረድ እያለ ቢመጣም አልፎ አልፎ መቀስቀሱ፤ ህይወት ንብረት ማጥፋቱ አልቀረም። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ የአከባቢው የመንግስት ሰራተኛ የሚሉትም ይህንኑ ነው።

ባለፈው ሳምንት ታህሳስ 24 የተጀመረው ግጭት ያጠፋው የሰው ህይወት 4 እንደሆነ የነገሩን አንድ የአከባቢው ነዋሪ ቤቶች አሁንም ድረስ በእሳት እንደያያዙ ነው የሚገልጹት።

በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ተወካይ ለማግኘት ያደረግነው ሰፊና አድካሚ ጥረት በመጨረሻው ሰዓት የወንዶ ገነት ወረዳ የጸጥታና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀመሮ ሀዬሶን አገኘንና ጉዳዩ በሁለቱ ብሄረሰቦች መሃል የተቀሰቀሰ ግጭት ሳይሆን የግለሰቦች ጸብ እንደሆነ ገለጹልን።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ