1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ ያገረሽው የጥላቻ እርምጃ

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2005

የአፍሪቃ ኅብረት (አንድነት ድርጅት) 50ኛ ዓመቱን ባከበረበት የሳምንት ማለቂያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በጆሐንስበርግ መዳረሻ፤ ሁከት ያገረሸበትና የጥላቻ እርምጃ የተወሰደበት ድርጊት ፤ አሳሳቢ መሆኑን የተለያዩ የዜና አውታሮች ገልጸዋል። የደቡብ አፍሪቃ

https://p.dw.com/p/18gxz
ምስል DW

መንግሥት፣ በትናትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ ፣ የውጭ ተወላጆች ሱቆችን እስከመዝረፍ እርምጃ መወሰዱ ፍጹም የወንጀል ተግባር እንጂ፤ የወጭ ዜጎችን ከመጥላት የመነጨ አይደለም የሚል የመነጨ አይደለም ማለቱ ተጠቅሷል።

ስለደቡብ አፍሪቃው የሁከት ማገርሸትና በዚያ ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይዞታ ፣ በጆሐንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያውያንን ማኅበረሰብ ዋና ጸሐፊ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

የተገደሉት የደቡብ አፍሪቃ ተወላጆች ባይሆኑም፤ የ 2 የጎረቤት አገር ተወላጆች ህይወታቸው በሰው እጅ መጥፋቱ ነው ፣ ሁከቱን የቀሰቀሰው ተባሏል። ሁለት ሌሊቶች በተከታታይ በውጭ ተወላጆች ንብረት ላይ ዘረፋ መካሄዱ ፤ እ ጎ አ በ 2008 ዓ ም ለ 62 የውጭ ተወላጆች መዘረፍ፣ መደብደብና መገደል ፣ ሰበብ የሆነው በውጭ ተወላጆች ላይ ያደረ ጥላቻ አገረሸ ወይ የሚል ጥያቄ ማስሰንዘሩ አልቀረም። ፖሊስ እንዳስታወቀው በ2 ቀናት ውስጥ 54 ያህል ሰዎች ናቸው ተይዘው የታሠሩት። ለሁከቱ ማገርሸት በእርግጥ ሰበብ ምክንያቱ ምን ይሆን? ከቅርብ ሁኔታውን የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያን ምን ይላሉ? በጆሐንስበርግ፤ ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዋና ጸሐፊ አቶ ደረጀ መኮንን--

ግድያ ፈጽሟል ተብሎ የተያዘው ሶማሊ፤ ንብረቱን ሊዘርፉ በመጡ ሰዎች ላይ መተኮሱን አልካደም። ይሁንና ድርጊቱ የተፈጸመበት ወቅት፤ አጋጣሚው፣ የአፍሪቃ አቀፍነትን ስሜት የሚያንጸባርቅ አልመሰለም። ግድያውም ዘረፋውም የተፈጸመው የአፍሪቃ ኅብረት 50ኛ ዓመቱን ባከበረበት የሳምንቱ ማለቂያ ላይ ነው። የደቡብ አፍሪቃ ህዝብ ስለአፍሪቃዊነት ስሜት ፤ ስለአፍሪቃ ኅብረት ግንዛቤው እስከምን ድረስ ይሆን?

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ