1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን እና የኢጋድ ስብሰባ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 9 2010

ደቡብ ሱዳን ውዝግብ የቀጠለባትን የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖችን እንደገና ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ የማምጣት ዓላማ ይዞ የተነሳ  አዲስ የውይይት ዙር ዛሬ በአዲስ አበባ የአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ ተጀመረ።

https://p.dw.com/p/2pa5Q
Rebellen in Südsudan
ምስል Reuters/G. Tomasevic

እልባት የጠፋለት የደቡብ ሱዳን ቀውስ

በተቀናቃኞቹ ወገኖች መካከል በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓም ተደርሶ የነበረው  የሰላም ስምምነት ባለፈው ዓመት ከከሸፈ ወዲህ የሀገሪቱ ህዝብ ስቃይና መከራ እየባሰ ሄዷል። ለዚህም የፖለቲካ መሪዎች ተጠያቂዎች ናቸው በማለት በስብሰባው ንግግር ያሰሙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወቅሰዋል።  የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ፣ በምህጻሩ ኢጋድ በጠራው በዚሁ ጉባዔ ላይ የአፍሪቃ ህብረት አባል መንግሥታት፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ እንዲሁም፣ ከሁሉም የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ ደቡብ ሱዳናውያን ተሳታፊዎች ሆነዋል።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ