1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በይርጋ ጨፌ ፤ የአርሶ አደሮች የመፈናቀል ሥጋት

ረቡዕ፣ ኅዳር 3 2007

በደቡብ ኢትዮጵያ በጌዴዖ አካባቢ የይርጋ ጨፌ ወረዳ ኑዋሪዎች የሆኑ ወደ 400 የሚጠጉ አባዎራዎች፤ ከመሬታችን የመፈናቀል ብርቱ ሥጋት አድሮብናል አሉ። አርሶ አደሮቹ፤ ለጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት ባቀረቡት የአቤቱታ ማመልከቻና ለ DW በሰጡት መግለጫ፣

https://p.dw.com/p/1Dlz0
ምስል DW/A. Hahn

በከተማ መስፋፋት ስም ከመሬታችን ልንነቀል ነው ብለዋል። የይርጋ ጨፌ ከተማ ከንቲባ ግን እስካሁን መሬቱን ወደከተማ የማካለል ሥራ ተሠራ እንጂ ፣ አንድም ገበሬ ከመሬቱ አልተፈናቀለም ፣ ወደፊት የሚነሱበት ሁኔታ ሲፈጠር ግን፣ ተገቢው ካሣ ይከፈላቸዋል ማለታቸው ተጠቅሷል። ዝርዝሩን ---ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ