1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በወጣት ሴቶች ላይ የሚደርስ በደል በፀኃፊዋ ብዕር

ዓርብ፣ ነሐሴ 27 2008

ወጣትዋ ደራሲ ሴና ጎዳና ዱላ ጂጆ ትባላለች ። ሴና ገና ከጨቅላነትዋ ባደገችበት ማኅበረሰብ በሴቶች ላይ የሚካሄዱት ባህላዊም ሆነ ልማዳዊ ተፅኖዎች ስለሚያስጨንቃት በጥያቄነት በአዕምሮዋ ዉስጥ ይመላለሱ ነበር።

https://p.dw.com/p/1Juip
Briefpapier Tinte
ምስል Fotlia/rsester

ሴና ገና በለጋ እድሜዋ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጥታ ከከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ተቋም ማለትም ዩንቨርስቲን ተከታትላ አጠናቃለች። ሴና በዩኤስ አሜሪካ ከፍተኛ ተቋም የመጀመርያ ዲግሪዋን በማኔጅመንት ተመርቃለች። ያ በልጅነት ጀምሮ ሲያሳስባት የነበረዉ ያለድሜ ጋብቻ ጠለፋ አስገድዶ መድፈር በቤተሰብና በጎረቤት ልጃገረዶች ወይም ወጣት ሴቶች ላይ የሚደርሰዉን ድብደባና ጭቆና በማስመልከት የዛሬ ዓመት ለህትመት ያበቃችዉ መጽሐፍዋ በተለይም በወጣት ሴቶች ላይ የሚደርሰዉን በደል ለዓለም ለማሳየት ያደረገችዉ ርምጃ እንደሆን ያሳያል። በእለቱ የወጣቶች ዝግጅት የሰሜን አሜሪካዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ደራሲዋን ወጣት ሴና ሴና ጎዳና ዱላ ጂጆን አነጋግሮ መሰናዳዎዉን ልኮልናል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ