1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኮንጎ የተባባሰዉ ግጭት

ሰኞ፣ ጥቅምት 25 2006

የኮንጎ ጦርና አማፂው M 23 ውጊያ ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ። በዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱት አማፅያን፤ ከኮንጎ መንግስት ጋር የተቋረጠዉን ድርድር ለመቀጠል፤ ትናንት የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቀዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/1ABTd
A Congolese army tank moves into position as they advance against the M23 rebels near the Rumangabo military base in Runyoni, 58 km (36 miles) north of Goma, October 31, 2013. Congo's army said on Thursday it was hunting rebels deep in the forests and mountains along the border with Rwanda and Uganda, the insurgents' last hideouts after they were driven from towns they seized during a 20-month rebellion. Picture taken October 31, 2013. REUTERS/Kenny Katombe (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: SOCIETY CIVIL UNREST POLITICS MILITARY)
ምስል Reuters/Kenny Katombe

ይህ የሆነዉ በተመድ ጦር የሚታገዙት የኮንጎ መንግስት ወታደሮች አማፅያኑን ለማባረር የጀመሩበትን ዉጊያ መግፋታቸዉ ከተገለፀ ከቀናት በኋላ መሆኑ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ወታደራዊ ኃይል በM-23 አማጽያን ላይ የከፈተዉ ጥቃት ትልቅ ስኬት ማሳየቱን መግለፁ ይታወሳል፤
የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ወታደራዊ ኃይል በምስራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱት የመጨረሻዎቹን የM23 አማፅያን ለማደን በያዘዉ ዘመቻ ገፍቷል። ከባድ ተኩስ መሰማቱ በአካባቢዉ ላይ ያሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ። የኮንጎ ወታደራዊ ኃይል እና የM23 አማፅያን በምስራቃዊ ኮንጎ ለደረሰዉ ከፍተኛ ጥፋትና ምስቅልቅል አንዳቸዉ ሌላኛቸዉን ይከሳሉ። በቡናጋና፣ ሙቡዚያና ሩንዮኒ ወደተባሉ በብዛት የሚገኙባቸዉ አካባቢዎች ላይ ባለፈዉ ረቡዕ ከፍተኛ ጥቃት ከተጣለ በኋላ አማጽያኑ ወደ ዩጋንዳ ድንበር ማፈግፈጋቸዉ ተነግሮአል። በተፈጠረዉ ከፍተኛ ዉጥረት አካባቢዉን ለቀዉ ከሸሹት ነዋሪዎች አንዱ፤

«ቦታዉን ለቀን ሸሽተናል። የመጣነዉ ከተራራዉ አካባቢ ነዉ። ለልጆቻችን የሚበላም ሆነ የሚለበር ነገር የለንም። ልጆቻችን በረሃብ ያልቃሉ።»
በዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱት አማፅያን፤ ከኮንጎ መንግስት ጋር የተቋረጠዉን ድርድር ለመቀጠል፤ ትናንት የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቃቸዉ የሃሰት እርምጃ ነዉ ሲል የኮንጎ መንግስት ዉድቅ አድርጓል። ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካንፓላ ላይ ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክና በM-23 አማጽያን መካከል ዕርቅ እንዲወርድ በሚካሄደዉ ሽምግልና ከሚሳተፉት የአማፅያኑ ወገን የሆኑት ቤትራንድ ቢስማዋ በጠላትነት የመተያየቱ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም እንዲያደርግ የዩጋንዳን መንግስት
ጠይቀዋል። ካንፓላ በተደጋጋሚ ሁለቱ የኮንጎ ተቀናቃኝ ኃይሎች የሰላም ድርድር የተካሄደበት ቦታ ቢሆንም መቋጫ ባጣዉ ጦርነትና ግጭት፤ የተጀመረዉ የዕርቅ ድርድር እስከ ዛሬ ፈር አለመያዙ እየታየ ነዉ። በሌላ በኩል ግን በሰሜናዊ ኪቩ አዉራጃ የመረጃ ሚንስትር ማሪየ ሻምሲ ከአማጽያኑ ጎን የተሰለፉ ዜጎችን ወደቤታቸዉ እንዲመለሱ ጠይቀዋል።
«አማጽያኑን የተቀላቀሉትን ወንድሞቻችንን ወደቤታቸዉ ተመልሰዉ እንዲመጡ እጠይቃለሁ። ተታለዉ ሄደዉ ነበር ግን አሁን ወደቤታቸዉ ተመልሰዉ መግባት ይችላሉ። ከዚህ በተጨማሪ እየተጠቋቆምን ይሄ የ M23 አማጺ አባል ነበርም አንባባል። እርስ በርስ እንዋደድ፤ ሁላችንም የኮንጎ ተወላጆች ነን፤ ሀገራችንን እንገንባ።»
የተባበሩት መንግሥታትና የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች፤ M-23 አማጽያን በሲቭሉ ህዝብ ላይ የጭካኔ ተግባር ፈጽመዋል አስግድዶ መድፈርና የመሳሰለውን አካሂደዋል፤ በ 10 ሺ የሚቆጠር ህዝብም ከቀየው እንዲፈናቀል ሰበብ ሆነዋል ሲሉ በተደጋጋሚ ወቅሰዋል።

GettyImages 174416940 A M23 soldier stands guard in the village of Kimbuba, in a M23 rebel-held territory, in the Democratic Republic of Congo on July 25, 2013. Rebels claimed on July 24, 2013 that they had killed more than 400 army troops since fighting resumed ten days ago in the Democratic Republic of Congo's volatile east, as each side accused the other of new attacks. AFP PHOTO / JUNIOR D. KANNAH (Photo credit should read JUNIOR D.KANNAH/AFP/Getty Images)
ምስል Junior D.KannahAFP/Getty Images)
Congolese soldiers rest while being deployed against the M23 rebels near Bunagana, north of Goma, November 1, 2013. Uganda called on the Congolese army and M23 rebels to cease fire on Friday as peace talks progressed in Kampala to end their 20-month conflict. While the rebels said they were ready for a peace deal, government forces vowed to pursue their military advantage and crush the rebellion in the Democratic Republic of Congo's mineral-rich east. REUTERS/Kenny Katombe (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: MILITARY CIVIL UNREST)
ምስል Reuters/Kenny Katombe

አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ