1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በክልልና በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት

ዓርብ፣ ጥር 30 2006

ሰሞኑን በአዲስ አበባና በክክሎ ከተሞች የነዳጅ እጥረት መከሰቱንና ይህም ተገልጋዮችን ማማረሩን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር ከአዲስ አበባ የላከዉ ዘገባ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1B4xS
ምስል DW/G. Faskhutdinow

በተለይ አዲስ አበባ የሚኖሩ ተገልጋዮች ለዶቼ ቬለ እንደገለፁት ነዳጅ ፍለጋ ጊዜያቸዉን ከማጥፋታቸዉ በተጨማሪ ሥራቸዉን በአግባቡ ማከናወን ተቸግረዋል። የንግድ ሚኒስቴር በበኩሉ በሀገሪቱ አንዳችም የነዳጅ አቅርቦት ችግር እንደሌለ በማመልከት ችግሩ በአጓጓዥ ኩባንያዎችና በነዳጅ ማደያዎች በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ገልጿል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ