1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በእነ እስክንድር ጉዳይ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ

ዓርብ፣ ግንቦት 3 2004

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍትኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት በተከሰሱት ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኛ ላይ ዛሪ ይሰጣል የተባለውን ብይን ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ። ዛሬ ያስቻለው ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የአመራር አባል አቶ

https://p.dw.com/p/14u3w
ምስል AP

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍትኛ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት በተከሰሱት ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኛ ላይ ዛሪ ይሰጣል የተባለውን ብይን ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ። ዛሬ ያስቻለው ፍርድ ቤት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የአመራር አባል አቶ አንዱ ዓለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በአሸባሪነት በተከሰሱ 24 ስዎች ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ ነበር ። ሆኖም ፍርድቤቱ ለ ሰኔ 14 ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ሂደቱን የተከታተለውን የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ታደሰ እንግዳውን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግሬዋለሁ።የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሸባሪነት በተከሰሱት በመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናትና በጋዜጠኛ እስክድር ነጋ ክስ ላይ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲሳዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አንዱአለም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክድር ነጋን ጨምሮ የሃያ-አራት ተከሳሾችን ጉዳይ የሚመከታተለዉ ፍርድ ቤት ዛሬ ብይን ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።አዲስ አበባ ያስቻለዉ የከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ሰወስተኛ ወንጀል የመሐል ዳኛ እንደሻዉ እንዳለ እንዳስታወቁት የተከሳሽ ጠበቆች ካቀረቡት የመከላከያ ሐሳብ ገሚሱ ሥላልተፃፈ ብዩኑ ወደ ሰኔ አስራ-አራት ተላልፏል። ካለፈዉ መስከረም ጀምሮ በታሠሩት ፖለቲከኛኞች ና ጋዜጠኛ ላይ የተመሠረተዉን ክስ በርካታ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃዉመዉታል።

ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ