1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

በኢንተርኔት ዋጋ ላይ የቀረበ ስሞታ

ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2011

በኢትዮጵያ እንደው ሳይታሰብ የኢንተርኔት አገልግሎት ድንገት ድርግም የማለቱ ነገር ዘንድሮም አልቀረም። ያለምንም ይፋዊ ምክንያት ከሰሞኑ ለቀናት ኢንተርኔት መቋረጡ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ቀስቅሷል። የኢንተርኔቱ አገልግሎት እያለም ቢሆን “ዋጋው አልቀመስ እያለ ነው” የሚል ስሞታም የሚያቀርቡም አሉ።

https://p.dw.com/p/3Kn90
Symbolbild NSA Überwachung Handy
ምስል imago/avanti

በኢንተርኔት ዋጋ ላይ የቀረበ ስሞታ

“የኢንተርኔት ዋጋ አላግባብ እየተቆረጠብን ነው” የሚል ስሞታ በሰፊው እየተደመጠ ነው። “የ100 ብር ካርድ ተሞልቶ፣ ያውም ብቅ ጥልቅ ለሚል አገልግሎት፤ ቶሎ ያልቅብናል” በማለት ተገልጋዮች ያማርራሉ። “ለጥቂት አገልግሎት ከፍተኛ ገንዘብ እንድንከፍል እየተገደድን ነው” ሲሉ ከሚያማርሩ የኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች መካከል አንዱ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ትችቶችን በመጻፍ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ አንዱ ነው።  

የኔትወርክ መቆራረጡ ከሚያደርሰው ኢኮኖሚያው ጉዳት በላይ ሀሳብን በነጻ መግለጽ ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው ይላል ጋዜጠኛው። የተማሪዎች ፈተና፣ ግጭት፣ የኃላፊዎች ጉብኝት እና ሌሎች ምክንያቶች እየተፈለገ ኢንተርኔት ከመዝጋት ሌላ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ያስፈልጋል ይላል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር ጋዜጠኛ ኤልያስን አነጋግሯል።     

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ዩሃንስ ገብረእግዚያብሔር

እሸቴ በቀለ