1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮ-ሱዳን ድንበር የሰዎች ዝውውር እና ችግሮቹ 

ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2011

ከኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራንና የሚመለከታቸው የመንግስት ስራ ሐላፊዎች እንዲሁም የሱዳን ገዳሪፍ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙበት የጋራ የምክክር መድረክ በመቐለ ተካሂዷል። እስካሁን በአካባቢው የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ሕጋዊ ማዕቀፍ ስላልተበጀለት ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የተጋለጠ ነው ተብሏል፡፡

https://p.dw.com/p/3FRWS
Äthiopien Sudan Jobsuche Mekelle Migration
ምስል DW/M. Hailessilasie

የኢትዮ-ሱዳን የጋራ የምክክር መድረክ

በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር አካባቢዎች የሰዎች ዝውውርን ሕጋዊና ድህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ የሁለቱም መንግስታት ትኩረት ይሻል ተባለ፡፡ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራንና የሚመለከታቸው የመንግስት ስራ ሐላፊዎች እንዲሁም የሱዳን ገዳሪፍ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የሀገሪቱ ባለስልጣናት የተገኙበት የጋራ የምክክር መድረክ በመቀሌ ተካሂዷል፡በምክክር መድረኩ ላይ እስካሁን በአካባቢው የሚደረግ የሰዎች እንቅስቃሴ ሕጋዊ ማዕቀፍ ስላልተበጀለት ለተለያዩ ሕገወጥ ተግባራት የተጋለጠ ነው ተብሏል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ባለፊት 10 ዓመታት ብቻ ከኢትዮጵያ ከ1 ነጥብ 5 ሚልዮን በላይ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጠው ተሰደዋል፡፡ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል። በትንሹ ባለፊት ዓመታት ከ1 ነጥብ 1 ቢልዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለሕገወጥ ደላሎች መከፈሉን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ