1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የከያንያን አስተያየት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 3 2009

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አብዛኛዉን የኢትዮጵያ ጉዳይ የሚዘግቡ መገናኛ ዘዴዎችን ትኩረት እንደሳበ ነዉ። ኢትዮጵያዉያን የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ምን ይላሉ?

https://p.dw.com/p/2RCXi
Äthiopien Das Hochland von Konso
ምስል picture-alliance/Mary Evans Picture Library/M. Watson

በኢትዮጵያ ጉዳይ የከያንያን አስተያየት

ሕዝባዊዉ ተቃዉሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣቱ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ርምጃ እየባሰ መጥቶአል። የብዙ ሠዎች ሕይወት ጠፍቶአል ፤ በርካታ ኃብትና ንብረትም ወድሞአል። 
ተቃዉሞዉን ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ከወሰዳቸዉ ርምጃዎች በተጨማሪ ባለፈዉ ሳምንት ማብቅያ ለስድስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጎአል። ተቃዉሞዉና የመንግሥት ርምጃ የብዙዉን የሃገሪቱን ኅብረተሰብ የእለት ከእለት እንቅስቃሴ እያወከ መሆኑም እየተነገረ ነዉ የኪነጥበብ ሰዎችም ከአብዛኛዉ ሕዝብ በተለየ መንገድ ያለመረጋጋቱ እንቅስቃሴያቸዉን እያስተጓጎለ ነዉ አንዳንዶች መፍትሄ በማፈላለግ ጊደት የኪነጥበብ ሰዎችን አሳታፊ መሆን አለባቸዉ የሚሉ አሉ።

አብዛኞች በግል ስናናግራቸዉ በግልጽ ቅሪታቸዉን አለ የሚሉትን ችግርና ይደርሳል የሚሉትን ተፅዕኖ ቢናገሩም በመገናኛ ዘዴ ላይ ወጥተዉ ግን በይፋ ለመናገር አይደፍሩም ። ጥቂት ከያንያንን አነጋግረን መሰናዶ ይዘናል። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ