1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደነገገ

እሑድ፣ መስከረም 29 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ዛሬ አስታወቀ። አዋጁ ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆይ ሲሆን ተግባራዊ የሆነውም ከትናንት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም አንስቶ መሆኑ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/2R3Wi
Äthiopien Trauer für gestorbenen Demonstranten
ምስል picture-alliance/AP Photo/K. Prinsloo

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ዛሬ አስታወቀ። አዋጁ ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆይ ሲሆን ተግባራዊ የሆነውም ከትናንት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም አንስቶ መሆኑ ተገልጿል። ሮይተርስ የዜና ወኪል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንን ጠቅሶ እንደዘገበው አዋጁ የተደነገገው ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች የተነሳውን እና የቀጠለውን አመጽ ለማስቆም ነው። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰላም እና መረጋጋት በአጭር ጊዜ ውስጥ መስፈን እንዳለበት ገልፀው ኢሕአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመወያየት እቅድ እንዳለውም መናገራቸውን  ሮይተርስ ዘግቧል።

Proteste in Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

አሶሺየትድ ፕሬስ የተሰኘው የዜና ምንጭ ደግሞ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ መግቢያ እና መውጪያዎች መዘጋታቸውን የዐይን እማኝ በስልክ እንደነገረው ዘግቧል። ለማለፍ የሚሞክሩ ተሽከርካሪዎች ላይም ከጫካ ውስጥ የሚወጡ ሰዎች የድንጋይ ሩምታ እንደሚያዘንቡ የዜና ምንጩ አክሎ ጠቅሷል። ባለፈዉ ዕሁድ በቢሾፍቱ ወይም በደብረዘይት ከተማ የኢሬቻ በዓል በሚከበርበት ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች ሞተዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በቀጠለው አመፅ የሕይወት መጥፋትና ከፍተኛ የንብረት መውደም መድረሱ ሰሞኑን ተዘግቧል። በሀገሪቱ አሁንም ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እና የስልክ አገልግሎት እንደተቋረጡ ናቸው።

ልደት አበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ