1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የሚታየዉ የመረጃ ክፍተት

እሑድ፣ ሚያዝያ 9 2008

የመገናኛ ብዙኃን እንደተቋምም ሆሙ ጋዜጠኞች በተናጠል ለሚያቀርቧቸዉ ዘገባዎች በቂ እና ዝርዝር መርጃ ማግኘታቸዉ ሚዛናዊ ዘገባን ለማቅረብ እንደሚረዳቸዉ ይታመናል። ብዙ ሃገራት የመረጃ ፍሰትን የሚያበረታታ ሕግ አጽደቀዋል።

https://p.dw.com/p/1IWjN
Media Information Literacy
ምስል DW/S. Didszuweit

በኢትዮጵያ የሚታየዉ የመረጃ ክፍተት

ኢትዮጵያም እንዲህ ያለዉ ሕግ ካላቸዉ ሃገራት አንዷ ናት። ጋዜጠኞችም ሆኑ የፕረስ ነፃነት የሚሟገቱ ተቋማት ሕጉ ከሕግነት በዘለለ በተግባር እንደማይገለጽ ይናገራሉ። የመረጃ ክፍተት መኖርም ሚዛኑን ያልጠበቀ፤ አልፎም የተለያየ እዉነት ያለ እሚመስል ዘገባ እንዲቀርብ ምክንያት እንደሚሆን ይታመናል። ከሕዝብ የሚገኘዉ መረጃ፤ ከተቃዉሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰነዘረዉ አቤቱታም ሆነ ከመንግሥት የሚሰማዉ ማብራሪያ መራራቁ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ከማመላከቱ ሌላ መረጃን በማዳረስ ዝብርቁን መስመር ማስያዝ ይችላሉ የሚባሉት የመገናኛ ብዙሃን በቂ እና ግልጽ መረጃን ከሚመለከተዉ አካል ባለማግኘታቸዉ በአንድ ጉዳይ የተለያየ እዉነት ያለ እንዲመስል የሚያደርጉ ዘገባዎች እንዲወጡ ምክንያት መሆኑ ይታያል። ሙሉዉን ዉይይት ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ