1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚሞተዉ ሰዉ ቁጥር ጨመረ  

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2014

ዶክተር ግርማ አባቢ እንዳሉት ባለፉት ሁለት ቀናት ህይወታቸው ካለፉት ታማሚዎች መካከል አብዛኞቹ አጋዥ የመንተፈሻ ቪንትሌተር በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ናቸው ብለዋል ።የጤና ሚንስቴር በኩሉ አሁንም ህብረተሰቡ ከህክምናው ይልቅ በተህዋሲው ላለመያዝ የሚያደርገውን ጥንቃቄ እንዲጨምር ሲል እየወተወተ ይገኛል ።

https://p.dw.com/p/40Pbq
Äthiopien Hawassa | Girma Ababi, Chairperson Ministry of Health's Science Advisory Group
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ጨመረ  

በኢትዮጲያ የኮረና ተህዋሲን ለመከላከል የሚደረገው ጥንቃቄ መቀዛቀዝና በአገር ደረጃ ያጋጠመው አጋዥ የመንተፈሻ ቪንትሌተር እጥረት በበሽታው ለሚሞቱት ሰዎች ቁጥር መጨመር ምክንያት እየሆነ መምጣቱን የጤና ባለሙያዎች ገለፁ። የኮረና ተህዋሲ ህመምተኞችን በማከም ሙያዊ ግዴታቸውን ለተወጡ የጤና ባለሙያዎች በሀዋሳ ከተማ በተካሄደው የምስጋና ዝግጅት ላይ በጤና ሚንስቴር የሳይንስና ቴክኒክ አማካሪ ቡድን ሰብሳቢና የኢትዮጲያ የግል ጤና ተቋማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ግርማ አካባቢ ባለፉት ሁለት ቀናት ህይወታቸው ካለፉት ታማሚዎች መካከል አብዛኞቹ አጋዥ የመንተፈሻ ቪንትሌተር በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ናቸው ብለዋል ።የጤና ሚንስቴር በኩሉ አሁንም ህብረተሰቡ ከህክምናው ይልቅ በተህዋሲው ላለመያዝ የሚያደርገውን ጥንቃቄ እንዲጨምር ሲል እየወተወተ ይገኛል።  


ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ