1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰብዓዊ መብት ይዞታ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ

እሑድ፣ ኅዳር 25 2009

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች፣ አዋጁ የህዝብ እንቅስቃሴን እና የመገናኛ ዘዴዎች ነፃነቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንኙነቶችን ገድቧል ሲሉ ይተቻሉ። ከአዋጁ በፊት እንደነበረው ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ቀጥሏል ።

https://p.dw.com/p/2Tfow
Äthiopien Unruhen
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰብዓዊ መብት ይዞታ 

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መተዳደር ከጀመረች ሦስተኛው ወር ሊገባ ጥቂት ቀናት ናቸው የቀሩት ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቃውሞዎች ተጠናክረው ከቀጠሉ በኋላ የተደነገገው ይህ አዋጅ በሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የዜጎችም ደህንነት እንዲረጋገጥ አድርጓል ሲል መንግሥት ይናገራል ። ይሁንና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች አዋጁ የህዝብ እንቅስቃሴን የመገናኛ ዘዴዎች ነፃነቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግንኙነቶችን ገድቧል ሲሉ እየወቀሱ ነው። ከአዋጁ በፊት እንደነበረው ጋዜጠኞች እና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና አባላት መታሰራቸው ቀጥሏል። የአዋጁን አፈፃፀም እንዲመረምር የተቋቋመው ቦርድ  በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሰው አመጽ ሁከት እና ብጥብጥብ በማስነሳት ተጠርጥረዋል የተባሉ ከ11 ሺህ 600 በላይ ሰዎች እንደታሰሩ ከ20 ቀናት በፊት አስታውቋል ። ተቃዋሚዎች ደግሞ የታሰሩት ቁጥር ከዚህም በላይ ነው ይላሉ ። የመርማሪ ቦርዱ አባላት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎችን አያያዝ ለመመርመር በጎበኟቸው ማዕከላት እስረኞቹ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ማንሳታቸውም ተገልጿል። ከመካከላቸው ፍርድ ቤት አለመቅረባቸው እና ቤተሰቦቻቸው እንዲጎበኟቸው አለመፈቀዱ ይገኙበታል። ከተደነገገ ሁለት ወር ሊደፍን ሁለት ቀናት በቀሩት በኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዴት ይገመገማል? የዛሬው እንወያይ መነጋገሪያ ርዕስ ነው ።የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉውን ውይይት ይከታተሉ ።

ኂሩት መለሰ 

ልደት አበበ