1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ ስለታቀደው ሀገር አቀፍ ምክክር አስተያየት ከተለያዩ ከተሞች

ማክሰኞ፣ ጥር 17 2014

በኢትዮጵያ ሊካሔድ በታቀደው አገራዊ ምክክር ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶይቸ ቬለ የሰጡትን አስተያየት አሰባስበናል። አስተያየት ሰጪዎች ስለውይይቱ ያላቸውን በጎ አመለካከት እና የተቃውሞ ሐሳብ አንስተው ሰንዝረዋል።

https://p.dw.com/p/463HG
Äthiopien Debre Markos City
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ስለ ሀገር አቀፉ ምክክሩ አስተያየት ከአዲስ አበባ

ኢትዮጵያ ዉስጥ  ሀገራዊ ምክክር እንደሚደረግ በተደጋጋሚ እየተገለጠ ነው። ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረገዉ ጦርነት ግን አሁንም አልተቋረጠም። አፋር ክልል አባላ እና አካባቢውን የትግራይ ተዋጊዎች መያዛቸውን የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ወቅት ስለታሰበው ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ  ምክክር  በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች የሰጧቸውን አስተያየቶች አሰባስበናል። የታቀደው ብሔራዊ ምክክር በተሳካ መልኩ የሚካሄድ ከሆነ እየደፈረሰ ላለው የሰላም  መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል ህዝቡ እምነቱን ይገልጻል። 
የዶይቼ ቬለ ስዩም ጌቱ ያነጋገራቸው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ብሔራዊ ምክክሩ እንዲሳካም አሳታፊነቱ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ይገልጻሉ።  ብሔራዊ የምክክር መድረክ በአገሪቱ ያሉትን የቆዩ የቁርሾ መነሻ ምንጮች እንደሚያስወግድ አንዳንዶቹ መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ውጤት አያመጣም ብለዋል። በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን ለብሔራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ነው የፈታናቸው ማለት የአሸባሪ ቡድኑ አባላት በምክክሩ እንደሚሳተፉ አመላካች ነው ያሉም አስተያየት ሰጪዎችን ዶይቼ ቬሌ አነጋግሯል።ከአዲስ አበባ፣ ከባሕርዳር፣ ከኦሮሚያ፣ከድሬዳዋና ከአሶሳ የተጠናቀሩ አስተያየቶችን ከታች ያሉትን ማገናኛዎች በመጫን ማድመጥ ትችላላችሁ።

ሰለሞን ሙጬ

ዓለምነው መኮንን 

ሥዩም ጌቱ 

መሳይ ተክሉ

ነጋሳ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ