1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአውሮፓ የወጣት ሥራ አጥነትና መፍትሄው

ማክሰኞ፣ ሰኔ 25 2005

ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የወጣት ስራ አጥነት ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማምተዋል ። ይሁንና የተመደበው ገንዘብ

https://p.dw.com/p/190pV
ምስል picture-alliance/dpa

ከችግሩ ስፋት አንፃር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም የሚል ትችት ቀርቦበታል ። ከዓለማችን አሳሳቢ ችግሮች አንዱ የሆነው ወጣት ስራ አጥነት ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ትኩረት ሰጥተው ከተነጋገሩባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ነበር ። መሪዎቹ ብራሰል ቤልጂግ ባካሄዱት የ2 ቀናት ጉባኤ በአባል ሃገራት ውስጥ እየተባባሰ ለሄደው ለዚህ ችግር ችግሩ መፍትሄ ይሆናል ያሉትን ውሳኔም አሳልፈዋል ። ይሁንና ውሳኔው ችግሩን ሊፈታ አይችልም የሚሉ ትችቶች ቀርበውበታል ። በአውሮፓ ትምህርቱና ችሎታው እያላቸው ሥራ የማያገኙ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄድ በእጅጉ እያሳሳበ ነው ።

Jugendarbeitslosigkeit
ምስል picture-alliance/dpa

ችግሩ ጎልቶ የሚታየውም የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ቀውስ ሰለባ በሆኑት የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ላይ ነው ። ከችግሩ ገፈት ቀማሾች ውስጥ የግሪክ ወጣቶች ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛሉ ። ከግሪክ ስራ አጥ 60 በመቶው ወጣት ነው ። በስፔይን 50 በመቶ በኢጣልያ ደግሞ 40 በመቶ ወጣት ስራ አጥ አለ ። ስራ አጥነት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል በሚባልበት በጀርመንም የወጣት ስራ አጦች ቁጥር እያደገ ነው ። በብሪታኒያም ችግሩ ከቀድሞው እየባሰ ሄዷል ። ብሪታኒያ ውስጥ በግሉ ዘርፍ በማህበራዊ ጉዳዮች አስተዳደርና አማካሪነት የሚሰሩት ዶክተር ብሬ ያያ ወጣት ስራ አጥነት በብሪታኒያ አሁን በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያብራሩልናል ።
ያም ሆኖ በንፅፅር ሲታይ ብሪታኒያ ጠንካራ ኤኮኖሚ ካላቸው የአውሮፓ ሃገራት የተሻለ የሥራ እድል የሚገኝባት ሃገር ናት ። በዚህ ምክንያትም በርካታ የአውሮፓ ወጣቶች ለስራ ወደ ብሪታኒያ መሄድን ይመርጣሉ ። ይህ ደግሞ እንደ ዶክተር ብሬ በብሪታኒያ ወጣቶች የስራ እድል ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው ብዙውን ጊዜ በአውሮፓ ሃገራት የስራ አጥነት መንስኤ የችግሩ መንስኤ ተደርጎ የሚነሳው ዓለም አቀፉ የገንዘብ ቀውሱ ያስከተለው የኤኮኖሚ እንቅስቃሴ ዝግመት ቢሆንም ፣ የየሃገሩ ስርዓተ ትምህርት ድክመትም ለችግሩ መባባስ አስተዋጽኦ በማድረግ ይጠቀሳል ። ዶክተር ብሬ ግን ዋነኛው የችግሩ መንስኤ ክፍት የስራ ቦታ መጥፋቱ ነው ይላሉ ። በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ስራ አጥነት ለመቀነስ የአውሮፓ ህብረት አዲስ እቅድ ነድፏል እቅዱም ወጣቶች ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ስራ ለማግኘት ብቁ ያደርጋቸዋል ተብሎ ይታመናል ። ባለፈው ሳምንት በአውሮፓ የወጣት ስራ አጥነት ላይ የመከሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መሪዎች ችግሩን ለመፍታት የሚውል 6 ቢሊዮን ዮሮ ለመመደብ ተስማምተዋል ። ይሁንና የተመደበው ገንዘብ ከችግሩ ስፋት አንፃር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም የሚል ትችት ቀርቦበታል ። ዶክተር ብሬ ያያም ገንዘቡ ችግሩን ያቃላል ብለው አያምኑም ።እንደ ዶክተር ብሬ አሁን ህብረቱ የመደበው ገንዘብ ለሶስት ጉዳዮች ነው የሚውለውየአውሮፓ ህብረት ወጣት እራ አጥነት ለመቀነስ የተስማማበት ገንዘብ ፣ የሚገኘው ከአባል ሃገራቱ ነው ። አባል ሃገራት የወጪ ቅነሳ እንዲያደርጉ ግፊት በሚደርገበት በዚህ ወቅት ገንዘቡ የሚገኝበት መንገድ ማሳሰቡ አልቀረም ።

Jugendarbeitslosigkeit Portugal
ምስል picture-alliance/ZB

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ