1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል ህወሓት ያወደማቸዉ ቦታዎች በፎቶ አዉደ ርዕይ

ዓርብ፣ ጥር 6 2014

በአማራ ክልል ለተፈፀመው ወረራና ጉዳት አለመደራጀትና እንደ ህዝብ አንድ ሆኖ አለመራመድ መሆኑ ተገለፀ፤ በምስራቅ አማራ በህወሓት የተፈፀመውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ባሳለፍነው ሳምንት በባሕር ዳር ተካሂዷል፡፡

https://p.dw.com/p/45XpG
Äthiopien Ausstellung zum Krieg in der Region Amhara
ምስል Alemnew Mekonnen

ኢትዮጵያዉያን ለመልሶ ግንባታ እጃቸዉን ሊዘረጉ ይገባል

በአማራ ክልል ለተፈፀመው ወረራና ጉዳት አለመደራጀትና እንደ ህዝብ አንድ ሆኖ አለመራመድ መሆኑ ተገለፀ፤ በምስራቅ አማራ በህወሓት የተፈፀመውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያሳይ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ ባሳለፍነው ሳምንት በባሕር ዳር ተካሂዷል፡፡
ባለፈው ሰኞ በጊዮን ሆቴል አደባባይ የተከፈተው የፎቶ አውደ ርዕይ ለተመልካቾች ክፍት ሆኖ ቆይቷል፡፡ የፎቶ አውደ ርዕዩን ከተመለከቱት መካከል የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪው አቶ ሙሉጌታ ነቃጥበብ ከአውደ ርዕዩ በአማራ ክልል የደረሰውን ኢኮኖሚያዊና ሰብአዊ ክስረት መረዳታቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ የዚህ ዓይነት ጉዳቶች እንዳይደገሙ ኢትዮጵያውያን ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምዳቸውን ሊያዳብሩ እንደሚገባም አቶ ሙሉጌታ አመልክተዋል፡፡
ከጎንደር እንደመጡ የነገሩን አቶ ተሸገር ወ/ሚካኤል በበኩላቸው በግብርናው ዘርፍ የደረሰው ጉዳት ልብ የሚያደማ እንደሆነ ከፎቶ አወደ ርእይው መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡ በፈረሱ ተቋማት ላይ መቆዘም ዋጋ የለውም ያሉት አስተያየት ሰጪው እንዴያውም ተባብረን በተሸለ ደረጃ በመገንባት እውነተኛ የድል ባለቤቶች መሆናችንን ማሳየት አለብን ብለዋል፡፡ ከአሜሪካ ሲያትል የመጡት አቶ ይርታቸው መኮንን በሰጡት አስተያየት በቀጣይም ተመሳሳይ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ አንድነትን ማጠንከር እንደሚያስፈልግ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ጌታቸው ጀንበርም “ወረራ የተፈፀመብን የጠላታችን ጥንካሬ ሳይሆን የእኛ የአንድነት መላላት ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ይርታቸው መኮንን የጥፋቱን መጠንና ስፋት በአንድ ቋንቋብቻ ሳይሆን የዓለም ታላላቅ የሚዲያ ተቋማት እንዲዘገቡትና ሁሉም ሊያውቀው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ህወሓት በአማራ ክልል በወረራ በቆየበት ወቅት በርካታ ኢሰባዊ ጉዳቶችን ማድረሱንና በቢሊዮን የሚገመት የንብረት ውድመትና ዝርፊያ መፈፀሙን የአማራ ክልል አመልክቷል፡፡

Äthiopien Ausstellung zum Krieg in der Region Amhara
ምስል Alemnew Mekonnen


ዓለምነው መኮንን 

አዜብ ታደሰ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ