1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የቦንብ ፍንዳታና የጉዳቱ መጠን

ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2002

በትግራይ ክልል ለኢትዮ ኤርትራ ድንበር ቅርበት ባላት አዲዳዕሮ ከተማ በሚገኝ አንድ ሻይ ቤት ቅዳሜ ዕለት የነጎደዉ ፈንጂ ለአምስት ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት መሆኑ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/N75K
የኢትዮ ኤርትራ ድንበር አካባቢምስል AP Graphics/DW

በዚህ ፍንድታ 20 ሰዎችም ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋዉ ሁኔታና የጉዳቱ መጠን ምን እንደሚመስል ወደአካባቢዉ ስልክ በመደወል የጉዳት ሰለባዎቹን ቤተሰቦች ያነጋገረዉ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ከድሬደዋ ዘገባ ልኮልናል። በማያያዝም ባለፈዉ ቅዳሜ በሰሜናዊ ትግራይ አካባቢ በተፈፀመዉ የቦምብ ፍንዳታ የኤርትራ መንግስት እጅ እንዳለበት የጠቆሙት የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ፀጋዬ በርሄ ድርጊቱ ምርጫዉን ለማደናቀፍ ነዉ ብለዉታል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የምታቀርበዉ ይህን መሰል ክስ ምን መነሻ ይኖረዋል? ይህና ሌሎች ጥያቄዎችን በማንሳት የምስራቅ አፍሪቃ የፖለተካ ተንታኝ የሆኑትን አቶ ዩሱፍ ያሲንን ያነጋገረዉ መሳይ መኮንን ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል፤

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ