1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትግራይ የመከላከያ ሰራዊት እንቅስቃሴ በድጋሚ ተስተጓጎለ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 30 2011

ከትግራይ ክልል ሽረ ተነስተው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ለመንቀሳቀስ የሞከሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማእከላዊ ዕዝ አባላት በዛሬው ዕለት በህዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴያቸው መገታቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3BCpj
Truppenabzug an der Grenze zwischen Äthiopien und Eritrea
ምስል DW/M. Haileselassie

በትግራይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንቅስቃሴ በድጋሚ ተስተጓጎለ

ከትግራይ ክልል ሽረ ተነስተው ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ለመንቀሳቀስ የሞከሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማእከላዊ ዕዝ አባላት በዛሬው ዕለት በህዝብ ተቃውሞ እንቅስቃሴያቸው መገታቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለDW ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደገለጹት 25 ኦራል ተብለው የሚታወቁ የመከላከያ ሰራዊት ትልልቅ መኪናዎች ከነጭነታቸው እንዲሁም አምስት የወታደራዊ መኮንኖች መኪናዎች ከጉዟቸው ተስተጓጉሏል፡፡ በክልሉ ከሳምንት በፊት ተመሳሳይ ክስተት የተስተዋለ ሲሆን በዚያ የሚኖሩ ዜጎች አሁንም የደህንነት ስጋት አለብን ይላሉ፡፡

ሚሊዮን ኃይለስላሴ 

ተስፋለም ወልደየስ 

አርያም ተክሌ