1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በትራምፕ ፖሊስ የአዉሮጳ ኅብረት አቋም

ሐሙስ፣ ጥር 25 2009

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ነገ ማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ ላይ ተሰብስበዉ በስደተኞች ጉዳይና በአሁኑ ወቅት ኅብረቱን ከዉስጥና ከዉጭ እየተፈታተኑ ባሉት አሳሳቢ ነጥቦች ላይ እንደሚወያይ ተገለፀ። የአዉሮጳ ካዉንስል ፕሬዚዳንት የዶናልድ ትራምፕ ፖለቲካዊ ርምጃ ለኅብረቱ አሳሳቢ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/2WsK3
Brüssel EU Gipfel Donald Tusk
ምስል Getty Images/AFP/J. Thys

M M T/ Ber.Brüssel(EU-Ratspräsident Tusk warnt vor Trumps Politik) - MP3-Stereo


የአዉሮጳ ካዉንስል ፕሬዚዳንት ቱስክ ቀደም ሲል ለኅብረቱ አባል ሃገራት በጻፉት ደብዳቤ በአሁኑ ወቅት በኅብረቱ ላይ የተጋረጡትን ስጋቶች እንዲሁም ከጉባዔዉ የሚጠበቁትን ነጥቦች በመግለጽ የመወያያ አጀንዳዎችን አስታዉቀዋል። ነገ ማልታ ላይ ስለ ስደተኞች ጉዳይ የሚካሄደዉ ዉይይት እንዳበቃ ብሪታንያን ሳይጨምር 27 ቱ የኅብረቱ አባል ሃገሮች ቀደም ሲል በተጠቀሱት በኅብረቱ በኩል ስላሉት ተግዳሮቶችና በተለይም ከአሜሪካ በኩል ስለመጣዉ ስጋት እንደሚወያዩ ይጠበቃል። የአዉሮጳ ካዉንስል ፕሬዚዳንት ዶናልድ ቱስክ ከዚሁ ጉባዔ ቀደም ብለዉ እንዳስታወቁት የአዲሱ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት የዶናልድ ትራምፕ ፖለቲካዊ ርምጃ ለኅብረቱ አሳሳቢ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። ዝርዝር ዘገባዉን የብረስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።


ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ