በቫቲካን የኢትዮጵያ ጳጳሳዊ ኮሌጅ 100ኛ ዓመት ተከበረ
ሰኞ፣ ጥር 4 2012ማስታወቂያ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን መቀመጫ በሆነችው ቫቲካን ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ጳጳሳዊ ኮሌጅ 100ኛ አመት በትናንትናው ዕለት ተከበረ። ከኢትዮጵያ እና ከኤርትራ ወደ ቫቲካን የተጓዙ ጳጳሳት፤ በጣልያን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል። ይኸው የጳጳሳት ማሰልጠኛ ኮሌጅ የተመሠረተው በጎርጎሮሳዊው 1919 ዓ.ም. ነበር። በዓለም ካሉ ካቶሊካውያን አብያተ-ክርስቲያናት በቫቲካን እምብርት ኮሌጅ ያላት ኢትዮጵያ ብቻ ነች። ተክለዕዝጊ ገብረየሱስ ይኸ "አስደናቂ እና የሚገርም ነው" ይላል።
ተክለዕዝጊ ገብረየሱስ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሠ