1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቤልጂየም የሽብር ጥቃት እቅድ መክሸፍ

ዓርብ፣ ጥር 8 2007

እስላማዊ አሸባሪዎች በቤልጂየም የፖሊስና ሌሎች ተቋማት ላይ ሊያደርሱት የነበረዉን ከፍተኛ የተባለ የሽብር ጥቃት የቤልጂየም ፖሊስ ትናንት ማምሻዉን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1ELl5
Anti-Terror-Einsatz in Belgien
ምስል picture-alliance/dpa/Hoslet

የቤልጂየም ፖሊስ በጂሃዲስትነት የጠረጠራቸዉን ሁለት ከሶሪያ የተመለሱ መሆናቸዉ የተገለጸ ጥቃት አድራሾች ሲገድል አንዱን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተነግሯል። ፖሊስ የሽብር እቅዱን ያከሸፈዉ ከብራስልስ መቶ ኪሎሜትር ርቀት ላይ ከጀርመን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘዉ የቨርቬርስ ከተማ ባካሄደዉ አሰሳ ነዉ። የቤልጂየም ጠቅላይ ሚኒስትር ፖሊስ የወሰደዉ ርምጃ መንግሥታቸዉ ሽብርን ማስፋፋት የሚሹትን ለመዋጋት መቁረጧን ያሳያል ብለዋል። ባለፈዉ ሳምንት ፓሪስ ላይ ከደረሰዉ የሽብር ጥቃት በኋላ ጀርመንን ጨምሮ አብዛኞቹ የአዉሮጳ ሃገራት ከፍተኛ ጥንቃቄና ቁጥጥራቸዉን አጠናክረዋል። የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌየኋላ