1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የባህርዳር ነዋሪዎች በፖሊስ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ

ሐሙስ፣ ግንቦት 22 2011

የሕጉ መላላትም ሌላው ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ተሳታፊ የነበሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎች «የፀጥታ አካሉ ራሱ የሚያሰማራቸው ባጃጆች የወንጀል ተባባሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3JVLv
Äthiopien Amhara Bajaj Taxi Besitzer Versammlung
ምስል DW/A. Mekonnen

በባጃጅ ለሚፈጸመው ወንጀል የፖሊስ አባላት ተጠያቂ ተባሉ

በባጃጅ ተሸከርካሪዎች በመታገዝ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን  መንስኤ እና መፍትሔ የሚመለከት ውይይት ዛሬ በባሕር ዳር ተካሄደ።  አሽከርካሪዎቹ ባሕር ዳር ከተማ በባጃጅ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂዎቹ የፖሊስ አባላት መሆናቸውን በስብሰባው ላይ ተናግረዋል። የሕጉ መላላትም ሌላው ምክንያት እንደሆነ አመልክተዋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ተሳታፊ የነበሩ የባጃጅ አሽከርካሪዎች «የፀጥታ አካሉ ራሱ የሚያሰማራቸው ባጃጆች የወንጀል ተባባሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል። ስብሰባውን የተከታተለው የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘገባ ልኮልናል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ