1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቡርኪና ፋሶ ጥቃት ሰዎች ተገደሉ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2011

ቤተ-ክርስትያን ላይ የደረሰዉን ጥቃት ተከተሎ የቡርኪና ፋሶ ደኅንነት ቢሮ ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት ከሟቾቹ መካከል የቤተ-ክርስትያኒቱ አንድ ቄስ ይገኙበታል። የፊታችን ረቡዕ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ቡርኪና ፋሶን ጨምሮ ማሊን እና ኒጀርን ለመጎብኘት ወደ ምዕራብ አፍሪቃ ይጓዛሉ።

https://p.dw.com/p/3HfCO
Burkina Faso Sicherheitskräfte
ምስል Getty Images/AFP/A. Ouoba

በሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ ዉስጥ በሚገኝ አንድ ቤተ-ክርስትያን ላይ በደረሰ ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ። የሃገሪቱ ደኅንነት ቢሮ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት ከሟቾቹ መካከል የቤተ-ክርስትያኒቱ አንድ ቄስ ይገኙበታል። ጆቦ ከሚባል ሰሜናዊ ቦርኪናፋሶ ከተማ 60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘዉ ቤተ-ክርስትያን ላይ ለደረሰዉ ጥቃት አካባቢዉ ላይ የሚንቀሳቀሱት አክራሪ ሙስሊሞች መሆናቸዉ  ነዉ የተነገረዉ። የፊታችን ረቡዕ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ቡርኪና ፋሶን ጨምሮ ማሊን እና ኒጀርን ለመጎብኘት ወደ ምዕራብ አፍሪቃ ይጓዛሉ። ባለፈዉ የካቲት ወር ጀርመንን የጎበኙት የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ሮህ ማርክ ካቦሬ አሸባሪነትን ለመዋጋት በቅርበት የትብብር ሥራ ለመስራት መስማማታቸዉ ይታወሳል።   

 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ