1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሶርያ ኬሚካዊ ጦር መሳርያ ጥቃትና የተመድ

ማክሰኞ፣ መስከረም 7 2006

የተመድ ዋና ፀሃፊ ባን ጊሙን በሶርያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በኬሚካላዊ መሳርያ ማለቃቸዉን በጥብቅ አወገዙ። ዋና ጸሃፊ ባን ይህን የገለጹት በሶርያዉ የእርስ በርዕርስ ጦርነት ጅምላ ጨራሽ መሳርያ ለጥቃት ጥቅም ላይ ዋለ ከተባለ በኋላ፤

https://p.dw.com/p/19jSg
U.N. chemical weapons experts prepare before collecting samples from one of the sites of an alleged chemical weapons attack in Damascus' suburb of Zamalka in this August 29, 2013 file photo. A report by U.N. chemical weapons experts will likely confirm that poison gas was used in an August 21 attack on Damascus suburbs that killed hundreds of people, U.N. Secretary-General Ban Ki-moon said on September 13, 2013. France's U.N. ambassador, Gerard Araud, told reporters that September 16, 2013 is the tentative date for Ban to present Sellstrom's report to the Security Council and other U.N. member states. REUTERS/Bassam Khabieh/Files (SYRIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST CONFLICT HEALTH)--eingestellt von haz
ምስል Reuters

የተመድ የኬሚካል ጦር መሳርያ ጉዳይ መርማሪ ቡድን በሶርያ ናሙና ወስዶ የምርመራ ዉጤቱን ይፋ ካደረገ በኋላ መሆኑ ነዉ።
የዛሪ ሁለት ወር ግድም ሶርያ መዲና ዳማስቆ አጠገብ የተጣለዉን የመርዝ ጋዝ ጥቃት ተከትሎ፤ የተመድ የኬሚላካዊ መሳርያ መርማሪ ቡድን፤ ከቦታዉ የወሰደዉን ናሙና መርምሮ ሳሪን የተሰኘ መርዘኛ ጋዝ ጥቅም ላይ መዋሉን ትናንት ማረጋገጡ ይታወቃል። የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንጊሙን፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸዉ ያለፈበት ይህ የጅምላ ጨራሽ መሳርያ፤ ጥቅም ላይ መዋሉን በጥብቅ አዉግዘዋል። ድርጊቱ የዓለም አቀፍን ደንብ የጣሰ የጦር ወንጀል ነዉ ያሉት። ባን፤ የተባበሩት መንግስታት የኬሚካል ጦር መሳርያ ጉዳይ ምሁራን፤ ያቀረቡትን የምርመራ ዉጤት ትናንት ይፋ ሲያደርጉ ፤ በሶርያ ህጻናትን ጨምሮ ፤ ከአንድ ሽህ በላይ ህዝብ ያለቀበት መርዘኛ የጦር መሳርያ ሳሪን የተሰኘ መርዘኛ ጋዝ መሆኑን አስታዉቀዋል።
«የመርመርማሪ ቡድኑ ያቀረበዉ ዉጤት ነጻና ምንም አይነት አድሎ ያልተደረገበት ነዉ። ዉጤቱ እጅግ ከፍተኛ እና የማያከራክር ነዉ። ለምርመራ ከቀረበዉ ደም 85 % ዉ ዉጤት ሴሪን የተሰኘዉ መርዘኛ ጋዝ ተገኝቶበታል። ከአካባቢዉ ላይ የወሰድናቸዉ ናሙናዎች የምርመራ ዉጤትም እንዲሁ ሳሪን መርዘኛ ጋዝ ተገኝቶበታል። አብዛኛዉ የጦር መሳርያ፤ ሮኬትና የሮኬት ተሸካሚ ላይ የተገኘዉ የምርመራ ዉጤትም እንዲሁ ፤ ሲሪን የተሰኘዉ መርዘኛ ጋዝ እንዳለበት ተረጋግጦአል። የምርመራ ዉጤቱ ከደብዛዛ ማረጋገጫ እና ጥርጣሪ እጅግ የራቀና እርግጠኛ መልስ ነዉ። ድርጊቱ በጎአ 1925 ዓ,ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የፀደቀ ሕግ የተጣሰበት፤ እጅግ ግዙፍ የሆነ የጦር ወንጀል ነዉ። በጎአ 1988 ዓ,ም የኢራቁ ሳዳም ሁሴይን ሃላብያ ከተማ ጅምላ ጨራሽ መርዘኛ ጋዝ፤ ሲቪል ማህበረሰብ ላይ ከጣለ ወዲህ፤ እንዲህ አይነቱ ጥቃት ሲዘነዘር የሶርያዉ ሁለተኛ መሆኑ ነዉ»
የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ትናንት የምርመራዉን ዉጤት ይፋ ሲያደረጉ፤ ለወንጀሉ ተጠየቂ ማን እንደሆነ የገለጹት ነገር የለም። ከተመድ ይፋዊ መግለጫ በኋላ የዓረቡ ዓለም መንግስታት፤ ለድርጊቱ አስፈላጊዉ እርምጃ እንዲደረግ ፤ጠይቀዋል። የሙስሊም ሃገራት ጉባኤ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ «OIC » ዛሪ እንዳስታወቀዉ በሶርያ ነሐሴ 15 የተጣለዉ የመርዘኛ ጋዝ ጥቃት፤ የጦር ወንጀል እና በስብዕና ላይ የተፈጸመ ከባድ የወንጀል ድርጊት ነዉ። በመሆኑም የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል ነዉ ያሉት ። የጀርመኑ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተርቬለ በበኩላቸዉ፤ ወንጀሉ ዓለም አቀፍ ወንጀል መርማሪ ፍርድ ቤት መቅረብ ይኖርበታል ሲሉ ጥሪያቸዉን አሰምተዋል። ጥቃቱ ከአሳድ መንግስት በኩል መጣሉን በመግለፅ ላይ ያለችዉ የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የፀጥታ ጉዳይ ዋና አማካሪ ሱዛን ራይስ ፤ የሶርያዉን የኬሚካል ጦር መሳርያ ጉዳይ መርማሪዎቹ፤ ስለጥቃቱ ምንነት እንጂ፤ ጥቃቱ ማን ጣለ የሚለዉን ሃላፊነት መመርመር ሥራቸዉ አልነበረም ሲሉ በአሳድ መንግስት ላይ ሃላፊነቱን ጥለዋል።
የአሳድ መንግስትና ፤ ተቃዋሚዎቻቸዉ የሚወነጃጀሉበት የሶርያዉ የመርዘኛ ጋዝ ጥቃት፤ ወደ 400 ህጻናትን ጨምሮ ከ 1000 ሽ ሰዎች በላይ ህይወታቸዉን አጥተወል።
ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ፤ በሶርያ የሚገኘዉ የኬሚካላዊ ጦር መሳርያ እንዲወድም ከተስማሙ በኋላ፤ የአሜሪካ ዛቻ ባለመፈፀሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እፎይታን አስከትሎአል። በሩስያ እና በዩኤስ አሜሪካ ስምምነት መሰረት ሶርያ በአንድ ሳምንት ግዜ ዉስጥ ያላትን የኬሚካላዊ መሳርያ አይነት እና መጠን በዝርዝር ማቅረብ ይኖርባታል። ከዝያም እስከ መጭዉ የአዉሮጳዉያኑ 2014 ዓ,ም አጋማሽ ድረስ በሶርያ ያለዉ የኬሚካዊ ጦር መሳርያ መዉደም ይኖርበታል። ይህ ዉል በሶርያ በኩል በተባለዉ ግዜ ገቢራዊ ካልሆነ ዩናይትድ ስቴትስ በአሳድ መንግስት ላይ እርምጃ እንደምትወስድ እያስጠነቀቀች ነዉ።

አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ

United Nations Secretary-General Ban Ki-moon speaks during a news conference at the United Nations Headquarters in New York, September 9, 2013. In a bid to help the U.N. Security Council overcome its "embarrassing paralysis" on Syria, Ban said on Monday he may ask the council to demand that Damascus move its chemical arms stocks to sites where they can be safely stored and destroyed. REUTERS/Brendan McDermid (UNITED STATES - Tags: POLITICS CONFLICT)--eingestellt von haz
ምስል Reuters
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ