1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት ይቁም!

ረቡዕ፣ ኅዳር 17 2001

አሉአል ኮች ገና የ13ዓመት ታዳጊ ሳለች ነዉ በነፍጥ መግደልን የተማረችዉ። የደቡብና ሰሜን ሱዳን ዘመን ያስቆጠረ የእርስ በርስ ጦርነት የወለዳት የጫቃ ሽምቅ ተዋጊ።

https://p.dw.com/p/G1sM
በህግ አምላክ!
በህግ አምላክ!ምስል dpa
አሁን 36ዓመቷ ሲሆን ከመንግስት ወታደሮች ጋ ስትዋጋ ያሳለፈችዉን ሰቆቃ ስታስታዉስ ትንሽም ስቅጥጥ አይላትም። ይልቁንም ባሏ የሞተባት ኮች አሁን ቤተሰቧን ለመደገፍ የምታደርገዉን ትግል ስትናገር እንባዋ ባይኗ ግጥም ይላል።