1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሱዳን የአብዪ ግዛት ዉጥረት እና መፍትሄዉ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 16 2001

በሰሜን እና ደቡብ ሱዳን የዉዝግብ መነሻ የሆነዉ የአብዪ ግዛት ጉዳይ ትናንት ዴንሃግ ኔዘርላንድ በተሰየመዉ አለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት ዉሳኔ አግኝቶአል።

https://p.dw.com/p/Ivqt
በጦርነት የተፈናቀሉ ሱዳናዉያንምስል ullstein bild - Nico Schmidt

ጉዳዩ ወደ አለም አቀፍ ፍርድ ቤት የተላለፈዉ የግዛቱን ድንበር እንዲከልል ተቋቁሞ የነበረዉ የድንበር አካላይ ኮሚሽን ባለፈዉ አመት ባቀረበዉ ሃሳብ ላይ ባለመስማማት በተነሳዉ ብጥብጥ በርካታ ህዝብ ስለሞተ እንዲሁም ከተፈናቀለ በኻላ የካርቱም መንግስት እና የደቡብ ሱዳን ነጻ አዉጭ ንቅናቄ ባደረጉት ስምምነት ነበር። ዝርዝር ዘገባዉን ገበያዉ ንጉሴ ከብረስልስ አድርሶልናል

ገበያዉ ንጉሴ/አዜብ ታደሰ/አርያም ተክሌ