1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀልባ ስደተኞች በሜዲተራንያን ሰጠሙ

ሰኞ፣ ጥር 8 2009

ፍሮንቴክስ የተባለዉ የአዉሮጳ  የባህር ጠረፍ ጠባቂ ተቋም ከትናንት በስተያ ቅዳሜ በሊቢያ የባህር ዳርቻ ማለት በትሪፖሊና ሚዝራታ መካከል በአንድ አስተማማኝ ያልሆነ ጀልባ ታጭቀዉ ወደ አዉሮጳ ከመሻገር ከሞከሩ ከ100 ከሚበልጡ ስደተኞች መካከል ስምንት ሰዎች ብቻ በሕይወት መትረፋቸዉን አመለከተ።

https://p.dw.com/p/2VsHT
Mittelmeer Migranten und Flüchtlinge in Schlauchboot
ምስል picture-alliance/AP Photo/S. Diab


የጣልያን የባሕር ጠረፍ ጠባቂዎች ከፍሮንቴክስ ጋር በመተባበር  ባለፉት ሦስት ቀናት ሜዲተራንያን ባሕር ላይ ሲንሳፈፉ ለአደጋ የተጋለጡ 1,800 ስደተኞች ባህር ዉስጥ ከመስመጥ መታደጋቸዉ ተገልጿል።  ቅዳሜ ዕለት ተሰዳጆች ላይ የደረሰዉን አደጋ አስመልክቶ ሮም የሚገኘዉ ወኪላችን ተኽለዝጊ ገብረየሱስ፤ ኤጀንስያ አበሻ የተሰኘው የባህር ላይ ስደተኞችን የሚረዳው ግብረ ሰናይ ድርጅት መሥራችና መሪ አባ ሙሴ ዘርአይን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል። 


ተኽለዝጊ ገብረየሱስ


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ